ሬነሳንስ ት/ቤት አዲስ አበባ ለ ውድ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ ጉዳዩ፡- የክረምት ማጠናከሪያ ት/ት…

ሬነሳንስ ት/ቤት
አዲስ አበባ

ለ ውድ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ
ጉዳዩ፡- የክረምት ማጠናከሪያ ት/ት (SummerTutorial class) ይመለከታል፤
ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የክረምት ማጠናከሪያ ት/ት ከሐምሌ 6/2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 አምስት ክ/ጊዜ የሚማሩ ሲሆን በፕሮግራሙ ውስጥ ሁሉንም ተማሪዎች በማካተት ከመደበኛው የት/ት ይዘት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የተከታታይ የሶስት የክፍል ደረጃዎችን ትምህርት በጥልቀት በመስጠት፣ የተለያዩ የሀገር አቀፍ ፈተናና ሞዴል ጥያቄዎችን በመስራት በቂ ዕውቀት፣ ክህሎት እና ግንዛቤ በመፍጠር ለቀጣይ ዓመት የሀገር አቀፍ ፈተና (ESSLCE) በቂ ዝግጅት አድርገው እንዲቀርቡ እና ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ታስቦ የተዘጋጀ ፕሮግራም መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በፕሮግራሙ የሚሰጠው የት/ት አይነትለNatural Science ተማሪዎች English, Maths, Physics, Chemistry, Biology and Scholastic Aptitude test (SAT)
ለSocial science ተማሪዎች English, Maths, History, Geography, Economics, and (SAT) ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የክረምት ት/ት መርሃ ግብሩ በክላስተር የተመደቡ ቀራኒዮ መድሐኒያለም ቁ-1 ት/ቤት እና በት/ቤት ለተመደቡ በሬነሳንስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለሁሉም ግዴታ መሆኑን የአ.አ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በላከው የአፈፃፀም መመሪያ ላይ የተገለፀልን በመሆኑ ውድ የተማሪ ወላጆች ተማሪዎቹን በወቅቱ ወደ ት/ቤት እንድትልኩ እያሳወቅን ከሐምሌ 6/2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ክረምት ት/ቱ የማይመጣ ተማሪ ካለ ለመደበኛው ትምህርት መመዝገብ እንደማይችል እና ተማሪው ት/ቤት ለመቀየር ፈልጎ እንኳን መሸኛ ቢጠይቅ የማይሰጠው መሆኑን ትምህርት ቢሮ አሳውቆናል፡፡ በመሆኑም ከሰኞ ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም ጀምሮ ልጆዎትን ወደ ፕሮግራሙ እንዲልኩ እንገልፃለን፡፡   
-          የክረምት ት/ት የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 10/2018 ዓ.ም ይሆናል፡፡
-          ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ሲመጡ አስፈላጊውን የት/ት ግብዓት በማሟላት የደንብ ልብሳቸውን ለብሰው እና የት/ቤት መታወቂያ ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡  
ት/ቤቱ
❤13
July 10, 2026 3.7K 17