ለፈረንሣይ ቅርንጫፍ የአንደኛ ደረጃ እና ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤታችን እንዲሁም ለቂርቆስ ቅርንጫፍ ቅድመ መደበኛ ወይም ኬጂ ትምህርት ቤታችን ቤተሰቦች በሙሉ 👇
በሁለቱም ቅርንጫፍ የቅድመ መደበኛ እና የፈረንሳይ ቅርንጫፍ ደግሞ የአንደኛ ደረጃ እና የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤታችን የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ በይፋ መጀመሩን ለማብሰር እንወዳለን ።
በመሆኑም እንደሁልጊዜው ቀድመን የምንመዘግበው ነባር ተማሪዎቻችንን በመሆኑ ነባር ተማሪዎች ቀድማችሁ መመዝገብ አለባችሁ ።
ማሳሰቢያ ፦ ለነባር ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀነ ገደቡም ከነገ 10 /11/ 2018 ዓ.ም እስከ 15 / 11 / 2018 ዓ.ም ድረስ ሲሆን በእነዚህ ቀናት ብቻ መጥታችሁ መመዝገብ አለባችሁ።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ በኋላ ላይ ለሚፈጠረው መጨናነቅም ሆነ የቦታ እጥረት ክፍተት ትምህርት ቤቱ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን ።
መልካም ምሽት
July 16, 2026 1.5K 1