ነገ በዕለተ ቅዳሜ ሰኔ 27 ቀን የዓመቱ ስኬታማ የመማር እና የማስተማር ሥራችንን እና የድካማችንን ፍሬ የምናይበት ዕለት ነው ። በእርግጥ የራፊዲም ጥረት ፤ ትጋት እና ሂደት የዓመት ሳይሆን የዓመታት መሆኑ እርግጥ ነው ። ነገእንደ አምና እንደ ታች አምናው የቅድመ መደበኛ ተማሪዎቻችንን ልናስመርቅ ፣ የደረጃ ተማሪዎቻችንን ልንሸልም ፣ መምህራኖቻችንን ልናመሰግን ብሎም ዳግም ለሌላ አዲስ ዓመት እና አዲስ ቀን ልንዘጋጅ የዓመቱን ሥራችንን ልንዘጋ ነው ። ነገ ታላቁ ድግሳችን እንደ አምናው ሁሉ በተመሳሳይ በአምባሳደር ቲያትር ቤት ይደረጋል ። ታዲያ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች ጠዋት 1 : 30 በስፍራው በመገኘት ያለንን ሰዓት በአግባቡ እንድንጠቀም እናሳስባለን ። እንኳን ለዚች ቀን አደረሰን 👏
July 3, 2026 1.7K 2