ዛሬ የትምህርት ቤታችን የራፊዲም ታላቅ ድግስ ተደርጓል ። 👏👏👏👏👏👏👏 ቤተሰቦቻችን ይህንን ደስ… — Rafidim Youth Academy Public Relation Channel — TG.ME

ዛሬ የትምህርት ቤታችን የራፊዲም ታላቅ ድግስ ተደርጓል ።  👏👏👏👏👏👏👏 ቤተሰቦቻችን ይህንን ደስ የሚል እና የሚያኮራ ጉዞ ከእናንተ ጋር እያደረግን ስለሆነ እጅግ ደስተኞች ነን ። ሃገርን የሚሰራ ትውልድ የመቅረፅ ትልቅ ሃላፊነትን እየተወጣን እንዳለን እናምናለን ። ለዚህም ደግሞ ዛሬ ያስመረቅናቸው ህፃናቶቻችን እና በዬደረጃው ጀግና ተማሪዎች ሆነው አንደኛ የሚወጡት አዳጊ ልጆቻችን ፤  ከውጤትም በላይ የሆነው ደግሞ የተማሪዎቻችን ግብረ ገብነት ስኬቶቻችንን የምንለካባቸው ግልፅ ማሳያዎች ናቸው ። ዛሬ በአምባሳደር ቲያትር ቤት ከ500 በላይ ቤተሰቦቻችን የታደማችሁበት ፤ ኢትዮጵያን በትንሽ መድረክ ተወክላ ያዬንበት ቀን ነው ። በውዝዋዜ ፣ በድራማ በመዝሙሮች ቀናችን አምሮ ውሏል ። የታሪካዊ አርበኞች ታሪክ በልጆቻችን ጣፋጭ አንደበት ሲወሳ ነበር ። ዛሬ በሁለቱም ቅርንጫፍ 137 የኬጂ ተማሪዎችን መርቀን ወደ አንደኛ ክፍል ያሸጋገርንበት ዕለትም ነው ። ወደፊታችን ብሩህ መሆኑንም የትምህርት ቤታችን ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢንያም ግርማ የደረስንበትን ከፍታ ገልፀውልናል ። በዚህ መርሃግብር በዓመቱ በነበረው የክፍል ለክፍል ወድድር ከዬክፍላቸው አሸናፊ በመሆን ያጠናቀቁትን የምስክር ወረቀት የሰጠን ሲሆን ከሁለቱም ቅርንጫፍ ደግሞ የአሸናፊዎች አሸናፊ በመሆን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የወጡትን ተማሪዎች ሽልማት ሸልመናል ። በቀጣዩ  ዓመት የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ለመሆን ዛሬ ያስመረቅናቸው የኬጂ ተማሪዎቻችንም በቀጣይ ዓመት እንግዳ ነገር እንዳይሆንባቸው እና በደንብ እንዲላመዱት ብለን በማሰብ በዚህ ዓመት የክፍል ለክፍል ውድድር ማድረጋችን ይታወሳል ። በዚህም በዬቅርንጫፉ አንደኛ የወጡት ተማሪዎች ተሸልመዋል ። በዓመቱ ትምህርት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ በመሆን በዬክፍሉ ያጠናቀቁ ተማሪዎችን የወርቅ የብር እና የነሃስ ሜዳሊያ ሸልመናል ። ከአጠቃላይ ክፍሎችም አንደኛ በመሆን በሁለቱም ቅርንጫፍ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎቻችንን ደግሞ የዋንጫ ሽልማት ሸልመናል ። በዚህ አጋጣሚ እነዚህ በሁለቱም ቅርንጫፍ አንደኛ የሆኑት ተማሪዎቻችን ሴቶች ናቸው ። ወደፊት ለሃገራቸው ብዙ እንደሚያበረክቱ እናምንባቸዋለን ። እንኳን ለዚች ቀን አደረሰን ! ራፊዲም ትምህርት ቤት የእውቀት ቤት !

July 4, 2026 2.1K 1