ገጣሚና የዓይን ሕክምና ባለሙያዋ
እፀገነት ብርሃኔ "ያልተቋጨው ቁጭት" የተሰኘ የግጥም መድበሏን ለአንባቢዎች አበረከተች።
በቴፒ ከተማ ተወልዳ ያደገችው ገጣሚት እፀገነት ብርሃኔ በሙያዋ የዓይን ሕክምና ባለሙያ (ኦፕቶሜትሪስት) ናት።
በኩባ ሀገር የነበራትን የከፍተኛ ትምህርት ስኮላርሺፕ አጠናቃ ከተመለሰችበት ጊዜ አንስቶ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የዓይን ሕክምና ክፍል ውስጥ ህብረተሰቡን በቅንነት እና በታማኝነት በማገልገል ላይ ትገኛለች።
ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ኦፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማህበር ውስጥ የስራ አስፈጻሚ አባል በመሆን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊነቷን ከመወጣቷ ባሻገር፣ በተለያዩ የቴሌቪዥን መስኮቶች በመቅረብ ስለ ዓይን ጤና ጥበቃ የማህበረሰብ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ትሰራለች።
በተለያዩ ተቋማት የሚገኙ ሰራተኞች ነጻ የዓይን ምርመራ እና ሕክምና የሚያገኙበትን ሁኔታ በማመቻቸት ረገድም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክታለች።
በመስሪያ ቤቷም ሆነ በማህበሩ ዘንድ በዋናነት የምትታወቀው ለህብረተሰቡ ባላት የማህበረሰብ አገልግሎት እና የበጎ ፈቃደኝነት ፍቅር ነው።
ከብዙ በጥቂቱ ለህፃናት የዓይን ህክምና ምርመራ በማድረግ ነጻ መድሀኒት እና የመነጽር አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጋለች።
እንዲሁም በክረምት ወራት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እና በጤና ሚኒስቴር ትብብር ጊዜያዊ የህክምና መስጫ ጣቢያዎችን በማቋቋም ሁሉን አቀፍ የጤና ምርመራዎች እንዲካሄዱ የማስተባበር እና ለታካሚዎች ነጻ መነጽር የማደል ስራን በትጋት ስታከናውን ቆይታለች።
ይህች የማህበረሰብ አገልግሎት አርአያ የሆነችው ገጣሚት እፀገነት ብርሃኔ አሁን ደግሞ "ያልተቋጨው ቁጭት" የተሰኘ አዲስ የግጥም መድበሏን ለወገኖቿ አቅርባለች።
©ጌጡ ተመስገን
ሁሌም ማንበብ!

7
7August 24, 2026 2.6K 1