ለከፋ በዚህ ዘመን ሙሉ በሙሉ ባይጠፋም ግን በአንጻራዊነት ስናየው ከድሮ አንጻር እየጠፋ ያለ መጥፎ ባሕል ነው… — መጽሐፍቶችን በpdf📚 — TG.ME

ለከፋ

በዚህ ዘመን ሙሉ በሙሉ ባይጠፋም ግን በአንጻራዊነት ስናየው ከድሮ አንጻር እየጠፋ ያለ መጥፎ ባሕል ነው ለከፋ።

ዛሬ ብለከፍ ነው ለከፋን ማንሳቴ። "ድንቡሼ" አለኝ ልጁ... ከእንዲህ አይነቱ ለከፋ ለረጅም ጊዜ ስለራቅሁ ፈገግታን ጭሮብኝ በዝምታ መንገዴን ቀጠልሁ። እርሱም ቀጠለ... ምን ይዘጋሻል? ቆንጆ ብትሆኚ አታስቀምጪንም ነበር .... (ይሄን ንግግር ከማኀበራቸው ነው መሰለኝ የተጠመቁት)

አሁን ላይ የራሴን ስብዕና የገነባሁ ማንነቴን ሰዎች እና ይህ ዓለም ባስቀመጠው ሚዛን ለክቼ ስደሰት እና ሳዝን የምኖር ሰው ስላልሆንኩ ውስጤን አይጎዳውም። ለነገሩ ታዳጊ ሆኜም ቤተሰቦቼ ራሴን እንዳውቅ ስለረዱኝ ትዝ ይለኛል ሁሌ የምጠይቀው  ጥያቄ "እኔ ትምህርት እየተማርኩ ውዬ ስገባ ሁሌ ድንጋይ ላይ ተቀምጦ የሚውለው ልጅ እኔን ለማሸማቀቅ ድፍረት የሚኖረው ለምንድን ነው?" የሚል ነበር😁 የሰው ልጅ ስብዕና በብዙ ምክንያት ሊሠራ እንደሚገባው አድጌ ስረዳ እንደ ሀገር ብዙ የቤት ሥራ እንዳለብን ተገንዝቤያለሁ።

ትዝ ይለኛል ተማሪ ሆኜ "ነይ አንቺ" ያለኝን የሰፈራችን ልጅ "አይ አልመጣም" ስላልኩት ያቀመሰኝ የሞቀ ጥፊ🙈 በሰዓቱ በልጁ ፊት ማልቀስ ስላልፈለኩ ዝም ስለው ምን አይነቷ ትዕቢተኛ ነች! ብሎ ለቀቀኝ። እቤት ስገባ ለአጎቴ ነግሬው ወዲያውኑ ልጁን በማግኘት ቀጥቶ ሥርዐት አስያዘልኝ (አንዳንድ ባለ ፐርስፔክቲቮች ይህን ታሪክ ቢሰሙ የታሪኩን ዋና ጭብጥ በመቀየር "በቤት ውስጥ የአጎት መኖር ለሴት ልጅ ያለው ጠቀሜታ" የሚል ትምህርት ያወጡለት ነበር🙄) ለዚህ ይመስለኛል ችግሩ አብሮን የሚዘልቀው። ስላስከፋኝ ወንድ ሳወራ ስለጠቀመኝ ወንድ ማንሳት ምን የሚሉት ነው? ለእኔው ነው የሚነገረኝ ይሄ? ያውም የአባቴ ልጅ ሆኜ??!!!

የሚላከፉ ወንዶች ፋራ ናቸው!!! ሲያድግ ደግሞ አጥቂ!! የለከፋ ጥሩ ጎን የለውም!! ባሌን ያገኘሁት ለክፎኝ ነው ብላ interview ላይ የምትናገረው ሴት ደግሞ ትምህርት ያስፈልጋታል🙄 ባልጠፋ የጋብቻ ትምህርት ምነው አለች? ሆሆሆ

©ጽናት ወንደሰን

ሁሌም ማንበብ!
❤15✍2🙏1🤨1🤝1
September 1, 2026 877 1