Orthodoxy: post #852 — TG.ME

ይድርስ ለፍቅርትዬ ማዕዶት ፤

ይህንን ደብዳቤ የምፅፍልሽ ለትጋትሽ ፣ ለጽናትሽ ፣ ለብርታትሽ እንዲሁም በፈገግታሽ ውስጥ የሚሰማኝን ታላቅ ደስታ ና ላንች ያለኝ ክብር እና ፍቅር ለመግለጽ ብቻ ነው።

እንደ ባለሞያ በሕይወቴ ብዙ የማልረሳቸው እና ሁሌም ከምናቤ የማይሰወሩ  ከሕመማቸው ጋር ሲታገሉ የማውቃቸው ብዙ ጀግኖች እና በዚያ በጽኑ ሕሙማን ክፍል በሥራ ያሳለፍኩባቸው እነዚያ እጅግ እረጃጅም ሌሊቶች በቂ ምስክሮች ናቸው።  አንች በየቀኑ fight የምታደርጊውን ሕመም እንደባለሞያ በሚገባ እረዳለሁ ። እያንዳንዱ ሕመምሽን እንደ ባለሞያ ፊል አደርገዋል  /at least  I feel your pain through psychologically/ ብል ማጋነን አይደለም። ለዚህም በየቀኑ የምታገኛቸው የስራ ባልደረቦቸ ምስክር ናቸው፡፡

ስለሆነም በዚህ እጅግ ፈታኝ በሆነው የካንሰር ህመም ውስጥ እያለፍሽ አንቺ ግን ለሁላችንም የብርታት፣ የተስፋና የፈውስ ትልቅ ምልክት ሆነሻል። እናመሰግናለን። በዚህም ስለ አንች በግሌ ኩራት ይሰማኛል። አንችም በዚህ ጥንካሬሽ ልትኮሪ ይገባል። ለብዙዎች መጽናናትን ምክንያት ሆነሻልና።
በተጨማሪም በየቀኑ የምታሳይው የጽናት ፈገግታ በወላጆችሽ እና በወዳጆችሽ እንዲሁም በዚህ የሕይወት መንገድ እያለፉ ባሉ በየትኛውም እድሜ ለሚገኙ ጀግኖች ሁሉ ያለ ጥርጥር  በአንች ኩራት ይሰማቸዋል። በዚህም በብዙ ሺህ በሚቆጠሩ ሰዎች ልብ ውስጥ አዲስ ተስፋን እና የህይወት ብርሃንን እንደዘራሽ ፈጽሞ አልጠራጠርም።

ልጅነትሽ የጨዋታና የደስታ ጊዜ መሆን ሲገባው  ከከባድ ህመም ጋር መታገልሽን ስናይ ልባችን ቢታመምም 😥 የአንቺ አይበገሬነት ግን ሁላችንንም ያበረታል፤ ያጸናል። 

በድጋሜ  ይኼን ሁሉ ዓረፍተነገር የማስረዝመው አንች ለማጽናናት አይደለም። አንቺ ከህመምሽ በላይ ነሽ! የደከሙትን የምታበረች ተስፋ የቆረጡትን የምታነቃቂ እና እውነተኛው ጥንካሬ በትንሽ ሰውነት ውስጥም #ሊኖር እንደሚችል ለመላው ሕዝባችን በታላቅ ጀግንነት ያሳየሽ ብርቱ መምህር ነሽ።

በየቀኑ የምታልፊበት እያንዳንዱ ፈተና አልፎ ፤ ሙሉ በሙሉ ተፈውሰሽ፤  በፍቅርና በደስታ ተከበበሽ ህልሞችሽን ሁሉ አሳክተሽ ለማየት ያብቃን። 🙏

እግዚአብሔር የተሟላ ፈውስንና ጤንነትን እንዲሰጥሽ እንማጸናለን። በተረፈ ይኼን ለአፍታ እንኳ እንዳትዘነጊ እያንዳንዷ ቀን ለአንቺ የድል ቀን ናት! ሁልጊዜም ቢሆን በአንቺ እንኮራለን፤ እንወድሻለን! My formula for greatness in a human being is amor fati: that one wants nothing to be different, not forward, not backward, not in all eternity. Not merely bear what is necessary, still less conceal it... but love it.
               — Nietzsche
with regards;
Yalewayker  / Anesthetist/
#orthodoxy #ማዕዶት🙏
🥰2❤1
August 5, 2026 197 2