Orthodoxy: post #848 — TG.ME

ሥጋዌን/ incarnation/ የሰበከው መልአክ ገብርኤል !

ቅዱስ ቂርቆስ እና እናቱን ከእቶን እሳት የታደገውም እርሱ ነው። የነብያቱን የይወርዳል ይወለዳል ስብከት ፍጻሜ /ብስራት/ የነገረን መልአክ ገብርኤል ነው። ለዳንኤል እና ለሠለስቱ ደቂቅም የተላከ እርሱ ነው። እኛን ለማማለድ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ይኼው ቅዱስ መልአክ ገብርኤል ነው።

Gabriel is sent to announce the birth of Christ. It is not any angel, but one of the highest rank, who is entrusted with this mission - ክርስቶስን ለመውለድ የምስራች ለማብሰር የተላከው ገብርኤል ነው። ይህንን ተልዕኮ በአደራ የተሰጠው ማንኛውም መልአክ ሳይሆን ከሊቃነ መላእክት መላእክት ለአንዱ ለገብርኤል ነው።

— ኦሪገን ዘእስክንድርያ -አርጌንስ

Gabriel, who stands in the presence of God, was sent to bring the message of joy to the Virgin, and through her to all mankind ‑ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ገብርኤል ለድንግል ማርያም የምስራቹን መልእክት አመጣ ፤ ይህ የምስራች በእመቤታችን በኩል ለሰው ልጆች ሁሉ ተሰብኳል።

— ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘታኦማቱርጉስ

Gabriel, the pure one, was sent to the pure Virgin. He brought the message of peace, and the world received its Savior - ከንጹኃን አንዱ ገብርኤል ንጽሕት ወደሆነች ድንግል ተላከ ፤ የሰላምንም መልእክት አመጣ ፤ ዓለምም አዳኛዋን ተቀበለች።

— ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

#orthodoxy #St.Gabriel #Incarnation
🥰3👏1🙏1
July 26, 2026 247