ይኼን ያደረገ ቅዱስ ሚካኤል ነው፤
• ስለ ሙሴ ሥጋ ከዲያብሎስ ጋር የተከራከረው ቅዱስ ሚካኤል ነውና (ይሁዳ 1፥9)፤
• ለሕዝቡ ነጻነትን ይሰጥ ዘንድ ከፋርሱ ንጉሥ ጋር የተከራከረው ቅዱስ ሚካኤል ነውና (ዳን.10፥13)፤
• የበለዓም አህያ ወደ ፊት እንዳትኼድ የከለከላት፣ በልዓምም ያንን ክፉ ሥራ እንዳይሠራ የከለከለው፣ በለዓም የሚናገረውን ባላወቀ ጊዜ ዲዳይቱን አህያ ጥበብን ሰጥቶ እንድትናገር ያደረጋት ቅዱስ ሚካኤል ነውና (ዘኁ.22)፤
• የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ የተገለጠለትና ኢያሱ ወልደ ነዌ ከኢያሪኮ ሰዎች ጋር እንደ ምን መዋጋት እንዳለበት የነገረው ይህ ቅዱስ ሚካኤል ነውና (ኢያ.5-6)፤
• በአንዲት ሌሊት 185,000 አሦራውያንን የገደለ፣ አሕዛብን በተኙበት ያስቀረ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ነውና (ኢሳ. 37:36)፤
• ነቢዩ ዕንባቆምን ከአናብስቱ ጋር በጉድጓድ ለነበረው ለዳንኤል በንፋስ ሰረገላ የወሰደውም ቅዱስ ሚካኤል ነውና (ዳን.14:32-42)፡፡
ቅዱሳን መላእክትን ማመስገን የተገባ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ያለማቋረጥ ያመሰግኑታልና፤ ለሰው ልጆች ምሕረት ቸርነትን ያደርግ ዘንድም ይማልዱታልና፡፡ ዳግመኛም አጋንንትን ድል እናደርጋቸው ዘንድ የሚረዱን ናቸውና ቅዱሳን መላእክትን ከፍ ከፍ ማድረግ የተገባ ነው፡፡
— ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
#ከሚካኤል_በቀር_የሚያጸናኝ_የለም
#orthodoxy
3
1
1July 19, 2026 278 1