Orthodoxy: post #840 — TG.ME

ዋሕደ ባሕርይ ወአካል ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ኢየሱስ ክርስቶስ

“ሰው ካራቱ ባሕርያተ ሥጋና ፫ ግብራተ ባሕርይ፣ ለባዊትነት ነባቢትነት ሕያዊትነት ካላት ከነፍስ የተፈጠረ መኾኑ ሳይዘነጋ አንድ ሰው እንዲባል፤ ክርስቶስም ፍጹም ሰው የኾነ ፍጹም አምላክ መኾኑ ሳይዘነጋ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ማለታችን የማይካድ ነው። ይህንም የምንልበት ምክንያት መጻሕፍት በያንቀጹ የመለኮትንና የትስብእትን ተዋሕዶ በነፍስና በሥጋ ተዋሕዶ ከመሰሉ በኋላ ፩ዱ የሚል ቅጽል እንጂ ክልኤቱ የሚል ቅጽል የሚቀጽልለት ባለማግኘታችን ነው። ”

#መድሎተ_አሚን #orthodoxy
❤3🥰2👏1
June 26, 2026 349 1