Grade8 የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ ይፋ እንዳደረገው የዘንድሮውን የ8ኛ ክፍል ፈተና ከተፈተኑ 45,034… — Abenezer kidus (abini) — TG.ME

#Grade8

የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ ይፋ እንዳደረገው የዘንድሮውን የ8ኛ ክፍል ፈተና ከተፈተኑ 45,034 ተፈታኞች መካከል 29,466 (65.43%) ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል ሲያልፉ 15,568 (34.57%) ተማሪዎች ፈተናውን ማለፍ አልቻሉም።

የማለፊያ ነጥብ ለመደበኛ ተማሪዎች 50% ፤ ለአካል ጉዳተኞች ደግሞ 45% መሆኑ ተገልጿል።

ከ790 አስፈታኝ ትምህርት ቤቶች መካከል 111 (14%) ትምህርት ቤቶች ሁሉንም ተማሪዎቻቸውን ሲያሳልፉ፣ 15 (1.8%) ትምህርት ቤቶች ደግሞ አንድም ተማሪ ማሳለፍ እንዳልቻሉ ታውቋል።

ቢሮው " የፈተና ሂደቱ ጤናማና ከኩረጃ የፀዳ እንዲሆን በተለዩ ክላስተር ጣቢያዎች ፈተናዉ እንዲሰጥ ተደርጓል " ብሏል።

https://sidama.ministry.et/#/result
❤12👏2
July 25, 2026 9.6K 8