የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ውጤት ይፋ አደረገ ቢሮው ውጤቱን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ፤ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ክልላዊ 50 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ድጋፍ ለሚሹ ደግሞ 48 እና በላይ ማለፊያ ነጥብ ተቆርጦለታል ብለዋል። በዚህ መሠረት 8ኛ ክፍል መደበኛ፣ የግል፣ ማታ እና ርቀት ተብሎ ተከፍሎ ውጤቱ መቀመጡን ሀላፊው በመግለጫቸው አብራርተዋል። በመሆኑ አጠቃላይ 8ኛ ክፍል የተመዘገቡ 86 ሺህ 502 ሲሆኑ የተፈተኑ 78 ሺህ 203 ከእነዚህ ውስጥ 50ና በላይ እንዲሁም 48 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡና ቀጣይ ክፍል ያለፉ 47 ሺህ 307 ናቸው ብለዋል አቶ አብዮት። በዚህ መሠረት ክልላዊ ውጤት ከመቶ ሲታይ 60 ነጥብ 4 ነው ብለዋል። በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ 126 ሺህ 224 ሲሆኑ ፈተና የወሰዱ ደግሞ 110 ሺህ 566 ከእነዚህ ደግሞ ማለፊያ ነጥብ አስመዝግበው ወደ ቀጣይ 7ኛ ክፍል የተዛወሩ 70 ሺህ 584 ናቸው ሲሉም የቢሮ ሀላፊ አብራርተዋል። በዚህም ክልላዊ ውጤት በመቶ ሲገለፅ 63 ነጥብ 8 እንደሆነ ተገልጿል። የ8ኛ ክፍል በትምህርት ቤት ደረጃ ሲገለፅ 540 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተመሪዎችን ማሳፍ ሲችሉ 155 ትምህርቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳየታቸውን አቶ አብዮት ገልፀዋል። በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል 476 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ሲያሳልፉ 81 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አላሳለፉም ብለዋል ሀላፊው። አጠቃላይ ክልላዊ ውጤቱ ከአምና የትምህርት ዘመን ውጤት ጋር ሲነፃፀር የ8ኛ ክፍል 3 በመቶ በማነስ ተመዝግቧል ሲሉም የቢሮ ሀላፊ ተናግረዋል። ይህ አምና ክልላዊ ውጤት በመቶ 63 በመቶ እንደነበር ተገልጿል። በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል አምና ክልላዊ ውጤት 56 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2018 ደግሞ 63 ነጥብ 84 እንደሆነም ተገልጿል። ተማሪዎችም በዚህ ሊንክ ገብተው ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል። https://se.ministry.et/#/result https://se6.ministry.et/#/result
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ውጤት ይፋ አደረገ ቢሮው ውጤቱን… — Abenezer kidus (abini) — TG.ME
August 4, 2026 8.9K 69