አሁን ውጤታቸውን ማየት ይቻላል‼
ውጤት:- https://aa6.ministry.et/#/result
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% ሆኖ መወሰኑን የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
የአጠቃላይ ካውንስል አባላት ባደረጉት ስብሰባ ያጸደቋቸው የማለፊያ ነጥቦች ፡-
📌 ለመደበኛ ተማሪዎች፡ 50%
📌 ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች፡ 45%
📌 ለኦቲስቲክ፣ ዳውን ሲንድረምና ኢንተሌክቹዋል ዲሴቢሊቲ ላለባቸው ተማሪዎች፡ 40%
በ2018 ዓ.ም 84,257 ተማሪዎች በ199 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፣ የዘንድሮው ውጤት ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዓመታት የተሻለ እድገት አሳይቷል ተብሏል።
768 ትምህርት ቤቶች ፈተና አስፈትነው 543 ያህሉ ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ማሳለፋቸው ተገልጿል።
ተፈታኝ ተማሪዎች ይህን ሊንክ https://aa6.ministry.et/#/result በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

35
13
8
4
3July 6, 2026 12.6K 34