ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በሐምሌ ወር ከሶስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ በገቢዎች… — MoR West Addis Ababa (ምዕራብ) — TG.ME

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በሐምሌ ወር ከሶስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ
በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ወር 222,319,228.61 (ሁለት መቶ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ አስራ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሃያ ስምንት ከ61/100) ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 389,247,580.57 (ሶስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሚሊዮን ሁለት መቶ አርባ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ ከ57/100) ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 175.08 በመቶ ማሳካት መቻሉን የሐምሌ ወር ዕቅድ በገመገመበት መድረክ አስታውቋል፡፡
በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ወር የገቢ ዕቅዳችንን በስኬት ጀምረናል ይህንን አጠናክረን ማስቀጠል ይጠበቅብናል ያሉት የታክስ ስርዓት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ቢሊሱማ ባይሳ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ላይ በተለይም የውሳኔ አሰጣጥ ጥራትና የአገልግሎት አሰጣጥ ጉዳይ በትኩረት ማከናውን እንደሚጠበቅ አሳስበዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ከሰው ሃይል ከግብዓትና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር ያሉ ክፍተቶችን በመሙላት ስራዎቻችንን በቅንጅትና በትጋት ለመወጣት ቁርጠኛ መሆን እንደሚጠበቅብን የተቋማዊ አቅምና ድጋፍ ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ሂካ ባርባ ተናግረዋል፡፡
የወሩን ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የዕቅድና በጀት ክትትል ቡድን አስተባባሪ አቶ ጎሶምሳ ተሰማ የተከናወኑ ተግባራትን፤ ያጋጠሙ ችግሮችንና የተወሰዱ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በዝርዝር አቅርበው ውይይት በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ተችሏል፡፡
https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto
www.tiktok.com/@morwestaa
❤14
August 18, 2026 6.4K 1 4