በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ማሳወቂያ ላይ የግማሽ ቀን ስልጠና ተሰጠ በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ… — MoR West Addis Ababa (ምዕራብ) — TG.ME

በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ማሳወቂያ ላይ የግማሽ ቀን ስልጠና ተሰጠ
በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በአዲሱ ኦንላይን የገቢ ግብር ማሳወቂያ ላይ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የግማሽ ቀን ስልጠና ሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ተወካይና የታክስ ስርዓት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ቢሊሱማ ባይሳ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ አሳውቀው እንዲከፍሉ ለማስቻል ተቋሙ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ በመጥቀስ የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅን ተከትሎ የተደረጉ ለውጦች ላይ መሰል ስልጠናዎችን መስጠት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኤሌክትሮኒክስ ታክስ ማስታወቅ ቡድን አስተባባሪ አቶ ማንያዘዋል ካሳዬ እና የታክስ ስሌት ባለሙያ አቶ ቢኒያም ባሳ የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 መሠረት በታክስ ማስታወቂያዎች ላይ የተደረጉ ለውጦችን ማስገንዘብ እና የሚነሱ ጥያቄዎች ላይ በመወያየት ግልጽኝነት መፍጠር የስልጠናው ዓላማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው በዋናነት በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ስለሚቀርቡ የሂሳብ አያያዝና ሪፖርት፤ በየሶስት ወሩ የሚከፈል የገቢ ግብር፤ አማራጭ አነስተኛ ግብር እና ሌሎች ኦንላይን የታክስ ማስታወቂያ ላይ የተደረጉ ለውጦችን የሚመለከቱ ሲሆን ከግብር ከፋዮች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ሥራ አስከያጅ ወ/ሮ ሺሻይት አባዲ እና በባለሙያዎች ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
https://t.me/morwestaa
https://www.facebook.com/profile.php?id=100090259834322
https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto
www.tiktok.com/@morwest
❤7
August 28, 2026 3.9K 1 6