የ51ኛ ዙር የታክስ ከፋዮች ሞጁላር ስልጠና እየተሠጠ ይገኛል
በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራ ሂደት ለ51ኛ ዙር የታክስ ከፋዮች ሞጁላር ስልጠናን እየሰጠ ይገኛል፡፡
በክፍል አንድ ቀጥተኛ የሆኑ የታክስ አይነቶች ላይ ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን በሞጁል አንድ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር እና የውጪ መጋራት ላይ የታክስ ከፋዮች መረጃ አቅርቦት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ እንዳለ ኤልያስ፤ በሞጁል ሁለት ከንግድ ትርፍ የሚገኝ ገቢ ግብር እና ከቤት ኪራይ የሚገኝ ገቢ ግብር ላይ የታክስ ከፋዮች ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ ወርቁ ጋንታ፤ በሞጁል ሶስት ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ግብርን ቀንሶ ስለማስቀረት (ዊዝሆልዲንድ ታክስ) ላይ የታክስ ከፋዮች ትምህርት ባለሙያ አቶ ደጀኔ ከፋለ፤ በክፍል ሁለት ቀጥተኛ ያልሆኑ የታክስ አይነቶች ላይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስን በተመለከተ የታክስ ከፋዮች ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ ኃይለሩፋኤል ኑርጊ፤ የቴምብር ቀረጥ እና ሱር ታክስን በተመለከተ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ተፈሪ ዳምጤ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ስልጠናው ለተከታታይ ሁለት ሳምንት መሰጠቱን የሚቀጥል ሲሆን የክፍል አንድ ቀጥተኛ የታክስ አይነቶች ላይ ፈተና ተሰጥቷል፡፡ በክፍል ሁለት ቀጥተኛ ካልሆኑ የታክስ አይነቶች መካከል የኤክሳይዝ ታክስ እና በክፍል ሶስት የታክስ አስተዳደር ሞጁሎች ላይ በቀጣይ ሳምንት መሰጠቱን ይቀጥላል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
https://t.me/morwestaa
https://www.facebook.com/profile.php?id=100090259834322
https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto
www.tiktok.com/@morwestaa
11
1August 14, 2026 7.5K 6 7









