በሰኔና በሐምሌ ወር አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ላወጡ ድርጅቶች ስልጠና ተሰጠ
በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ላወጡ ድርጅቶች በመሠረታዊ የታክስ ህጎች ላይ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የታክስ ከፋዮች ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ ኃይለሩፋኤል ኑርጊ አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያወጡ ድርጅቶች ስለታክስ ግንዛቤ ኖሯቸው መብታቸውንና ግዴታቸውን እንዲረዱ ማድረግ የስልጠናው ዓላማ መሆኑን በመግለፅ አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያወጡ ድርጅቶች ሳያውቁ ወደ ቅጣት እንዳይገቡና ቀጣይ ማድረግ ስለሚገባቸው ተግባር አስረድተዋል፡፡
በስልጠናው ስለ ታክስ ምንነት፣ የደረሰኝ ህትመትና አጠቃቀም፣ ግብር ቀንሶ ስለማስቀረት (ዊዝሆልዲንግ) ታክስ፣ ስለተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ስለሂሳብ መዝገብ አያያዝና ሌሎች አዲስ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ያወጡ ድርጅቶች ማወቅ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ከታክስ ህጉ አንፃር ገለፃ አድርገዋል፡፡ ከግብር ከፋዮች ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
https://t.me/morwestaa
https://www.facebook.com/profile.php?id=100090259834322
https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto
www.tiktok.com/@morwestaa
20
3July 30, 2026 14.9K 5 11



