በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 አንቀጽ 86 መሰረት ከአንድ በላይ የንግድ መስክ (ዘርፍ) ገቢ የሚያገኝ ድርጅት ለእያንዳንዱ የተለየ የንግድ ስራ መስክ የተናጠል የሂሳብ መዝገብ፣ ደጋፊ ሰነዶች እና የግብር ማስታወቅያ መያዝና ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው መደንገጉ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም የ2018 ዓመታዊ የኦላይን ማሳወቂያ ክፍት እስከሚሆን ድረስ ዓመታዊ ለማሳወቅ የምትመጡ ድርጅቶች ከዚህ በታች በተያያዘው አዲሱ የማሳወቂያ ፎርም መሰረት መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ አጠቃቀሙን በተመለከተ https://www.youtube.com/watch?v=me5ZU_UxK-4 ያገኛሉ
18
1July 29, 2026 14.8K 8 383