ለ50ኛ ዙር የሞጁላር ሰልጣኞች የክፍል አንድ ፈተና ተሰጠ
በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራ ሂደት ለ50ኛ ዙር የታክስ ከፋዮች ሞጁላር ስልጠናን እየሰጠ ይገኛል፡፡
በክፍል አንድ ቀጥተኛ የሆኑ የታክስ አይነቶች ላይ ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን በሞጁል አንድ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር እና የውጪ መጋራት ላይ የታክስ ከፋዮች መረጃ አቅርቦት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ እንዳለ ኤልያስ፤ በሞጁል ሁለት ከንግድ ትርፍ የሚገኝ ገቢ ግብር እና ከቤት ኪራይ የሚገኝ ገቢ ግብር ላይ የታክስ ከፋዮች ትምህርት መሪ ባለሙያ አቶ ወርቁ ጋንታ፤ በሞጁል ሶስት ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ግብርን ቀንሶ ስለማስቀረት (ዊዝሆልዲንድ ታክስ) ላይ የታክስ ከፋዮች ትምህርት ባለሙያ አቶ ደጀኔ ከፋለ፤ በክፍል ሁለት ቀጥተኛ ያልሆኑ የታክስ አይነቶች ላይ ኤክሳይዝ ታክስን በተመለከተ የታክስ ከፋዮች ትምህርት ባለሙያ አቶ አሸብር ዳምጤ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ስልጠናው ለተከታታይ ሁለት ሳምንት መሰጠቱን የሚቀጥል ሲሆን የክፍል አንድ ቀጥተኛ የሆኑ የታክስ አይነቶች ላይ ፈተና የተሰጠ ሲሆን በክፍል ሁለት ቀጥተኛ ያልሆኑ የታክስ አይነቶች እና በክፍል ሶስት የታክስ አስተዳደር ሞጁሎች ላይ በቀጣይ ቀናት መሰጠቱን ይቀጥላል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
https://t.me/morwestaa
https://www.facebook.com/profile.php?id=100090259834322
https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto
www.tiktok.com/@morwestaa
12
5
1July 18, 2026 7.6K 5 7







