ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በሀምሌ ወር 263.57 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ገለጸ
…………
ነሀሴ 13 /2018 //የምስራቅ /አ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት//
ወ/ሮ ወርቅዓለም ተሾመ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ የገቢ እቅዱን 263.57 ሚልዮን በመሰበሰብ 102.50 በመቶ አፈጻጸም መመዝገቡን የገለጹት በዛሬ እለት የሀምሌ ወር የእቅድ አፈጻጸም ውይይት ሲያደርጉ ነው ፡፡ይህ ስኬት በየደረጃው ያሉ ሃለፊዎችና ሰራተኞች እንዲሁም ግብራቸውን በሃላፊነት የከፈሉ ግብር ከፋዮች ውጤት መሆኑን ገልጸው አመሰግነዋል፡፡ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የ2019 እቅድ የዝግጅት ምእራፍ ላይ በመሆኑ በቀጣይ ሊሰሩ በሚገባቸው አጠቃላይ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የገቢ አሰባሰብና፣የአገልግሎት አሰጣጥ እና የአሰራር ሂደቶች በሚያሳይ መልኩ ውይይት ትኩረቱን እንደሚያደርግ ተናግረዋል ፡፡
ወ/ሪት ፍሬህይወት ተፈራ የዕቅድና በጀት አፈፃፀም ክትትል ከፍተኛ ባለሙያ የሀምሌ ወር የስራ አፈፃፀም ሲያቀርቡ ቅ/ጽ/ቤቱ ከቀጥታ ታክሶች፤ ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች በአጠቃላይ 257.14 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 263.57ሚሊዮን በመሰብሰብ አፈፃፀሙ 102.50% መሆኑን በሪፖርታቸው አሳይተዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ከተሰበሰበው አጠቃላይ ገቢ ብር 263.57ሚሊዮን መካከል ብር 147.28 ሚሊዮን ከቀጥታ ታክሶች፣ብር 112.67 ሚልዮን ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች እንዲሁም ብር 3.62 ሚሊዮን ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች የተሰበሰበ መሆኑ ገልጸዋል።
ወ/ሮ ወርቅዓለም የ2019 የመጀመሪያ እቅድ የዝግጅት ምእራፍ ከወዲሁ የወሩን አቅድ በማሳካት የተጀመረ መሆኑን ጠቅሰዋል ፡፡ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የዓመቱን እቅድ ለማሳካት ሆነ የአገልግሎት አሰጣጡ የበለጠ ቀልጣፋ እንዲሆን ከወዲሁ ስራዎች መሰራት እንደሚገባ አንስተዋል፤ ለገቢው መሳካት ሆነ የተገልጋይ እርካታ ያመጣሉ ያሏቸውንም ሲጠቅሱ ገቢን በመሰብሰብ ሆነ ተገልጋይን ለማርካት በሚደረግ ጥረት የአሰራር ክፍተት ሲገጥም ችግሩን በመለየት በዕውቀት እና በተደራጀ ሀሳብ አሰራሩን ምቹ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በየደረጀው የሚገኝ አመራር ሆነ ባለሙያ በሚሰራቸው ስራዎች አዋጅ መመሪያና ደንብ መከተሉን ማረጋገጥ እንደሚገባም አጽንዖት ሰጥተዋል ፡፡
ስራ አስኪያጅዋ ሁሉም አመራርና ፈጻሚ የመልካም አስተዳድር ክስተቶችን በመለየት በጥብቅ ዲሲፒሊን መምራት፣የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል ገቢ ሊያስገኙ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል በማለት የነሀሴን እቅድ ለማሳካት የሚያስችሉ የትኩረት አቅጣጫዎችን አመላክተዋል ፡፡
በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የየዘርፉ ምክትል ስራ አስኪያጆችና በየደረጃው የሚገኙ የስራ ሀላፊዎች ማብራሪያ በሚሹ ጉዳዮች ላይ አስተያየትና ምላሽ ሰጥተዋል ፡፡የማኔጅመንት አባላቱም ዕቅዱን ለማሳካት ሆነ ተገቢዉን አገልግሎት ለግብር ከፋዩ ለመስጠት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል ፡፡
16
2August 19, 2026 7.7K 8