ተቀናሽ የሚደረጉ ወጪዎች ግብር የሚከፈልበትን ገቢ ለመወሰን የሚከተሉት ከጠቅላላ ገቢ ላይ ይቀነሳሉ በገቢ… — M.O.R East Addis Ababa Branch — TG.ME

ተቀናሽ  የሚደረጉ  ወጪዎች
ግብር የሚከፈልበትን ገቢ ለመወሰን የሚከተሉት ከጠቅላላ ገቢ ላይ ይቀነሳሉ
በገቢ ግብር አዋጅ የተመለከቱ ገደቦች እንደተጠበቁ ሆኖ በንግድ ስራ ገቢው ውስጥ የተካተቱትን ገቢዎች ለማግኘት፣ ለንግዱ ስራ ዋስትና ለመስጠትና የንግድ ስራውን ለማስቀጠል በግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ የተደረጉ አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎች፣
Ø በግብር ዓመቱ ለተሸጠ የንግድ ዕቃ (trading stock) የወጣ ወጪ፣
Ø በንግድ ስራው ላይ ሲውሉ ዋጋቸው የሚቀንስ የንግድ ስራ ሃብቶችና ግዙፋዊ ህልወት ለሌላቸው የንግድ ስራ ሃብቶች በግብር ዓመቱ የሚታሰበው ጠቅላላ የእርጅና ቅናሽ፣
Ø የንግድ ዕቃን ሳይጨምር ግብር ከፋዩ በዓመቱ ውስጥ የንግድ ስራ ሃብትን በማስተላለፍ የገጠመው ኪሣራ፡፡
Ø በሠራተኛው የጤና ዕቅድ መሰረት ቀጣሪ በተቀጣሪ ስም የሚከፍለውን የጤናመድን አርቦን ጨምሮ ለሠራተኛው የሕክምና አገልግሎት የሚያወጣው ወጪ ሲሆኑ በታክስ ህጉ የተፈቀዱ ሌሎች ዝርዝር ተቀናሽ ወጪዎች በመመሪያ ቁጥር 5/2011 ይመልከቱ  ፡፡
❤10
August 18, 2026 5.9K 8