የእግር ኳስ ታሪክን የጻፈው የፔሌ ማሊያ 4.9 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ የቀድሞው የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች… — Min Addis? — TG.ME

የእግር ኳስ ታሪክን የጻፈው የፔሌ ማሊያ 4.9 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ

የቀድሞው የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ፔሌ በ1958ቱ የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ የለበሰው ማሊያ 4 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ተሽጧል፡፡

በዚያ ዓለም ዋንጫ ብራዚል ስዊድንን በማሸነፍ የዋንጫው ባለቤት በሆነችበት የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ፔሌ ሁለት ግቦቸን አስቆጥሮ ነበር፡፡

በወቅቱ የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ ሲያሳካ የ17 ዓመት ወጣት የነበረው ፔሌ የዓለም ዋንጫን ማሸነፍ የቻለ በዕድሜ ትንሹ ተጫዋች ነው፡፡

በአጠቃላይ ሦስት ጊዜ ከሀገሩ ብራዚል ጋር የዓለም ዋንጫን ማሳካት የቻለ ሲሆን፥ በዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ግብ ያስቆጠረ በዕድሜ ትንሹ ተጫዋች (17) በመሆን አሁንም ድረስ ክብረወሰኑን ይዞ ይገኛል።

በ1986 የዓለም ዋንጫ ላይ ዲያጎ ማራዶና በእንግሊዝ ላይ 'የእግዜር እጅ' በመባል የሚታወቀውን ግብ ሲያስቆጥር የለበሰው ማሊያ በ2022 በ7 ነጥብ 1 ሚሊየን ፓውንድ መሸጡ ይታወሳል፡፡

የፔሌ ማሊያ ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋች ማራዶና ቀጥሎ ከፍተኛ ዋጋ የወጣለት የእግር ኳስ ማሊያ ሆኗል።
@min_ddis
❤6👍2💯2
July 19, 2026 2.8K 1