ከሊዮኔል ሜሲ ጋር በፎቶ የተነሳው ህጻን ላሚን ያማል መሆኑ ዩኒሴፍ የእውነተኝነቱን ምስክርነት ሰጠ
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ሲዘዋወር የነበረውና ታዋቂው የእግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ አንድን ህጻን ሲያጥብ የሚያሳየው ፎቶግራፍ እውነተኛ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ይፋዊ መግለጫ ሰጥቷል። በፎቶው ላይ የሚታየው ህጻን የስፔኑ ወጣት ኮከብ ላሚን ያማል መሆኑ ተረጋግጧል።
ይህ ታሪካዊ ፎቶግራፍ የተነሳው ከ18 ዓመታት በፊት በዩኒሴፍ (UNICEF) የገቢ ማሰባሰቢያ የበጎ አድራጎት ፕሮግራም ላይ እንደነበር ተገልጿል። በወቅቱ ገና ህጻን የነበረው ላሚን ያማል ከእናቱ ሺላ ጋር በመሆን ከሊዮኔል ሜሲ ጋር እንዲገናኝ የተደረገ ሲሆን፣ ፎቶግራፉን ያነሳው ታዋቂው ጆአን ሞንፎርት (Joan Monfort) መሆኑ ታውቋል።
ዩኒሴፍ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ ሁለቱ የእግር ኳስ ኮከቦች በአሁኑ ወቅት በሜዳ ላይ ከሚያሳዩት ድንቅ ብቃት ባሻገር፣ ከሜዳ ውጪም የዩኒሴፍ የበጎ ፈቃድ አምባሳደሮች በመሆን በመላው ዓለም ለሚገኙ ህጻናት መብትና ደህንነት በጋራ እየሰሩ እንደሚገኝ በኩራት ገልጿል።
በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ተጫዋቾች በዓለም ዋንጫ ፍጻሜ እሁድ ይፋለማሉ።
@min_ddis
13
3
1
1
1July 17, 2026 2.7K 5


