በምዕራብ ሸዋ ዞን እና በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ መንግስት መር ጭፍጨፋ ሊካሄድ ነው!
ከነሃሴ 12/2018 ዓ/ም ጀምሮ በምስራቅ ወለጋ ዞን አንገር ጉትን ከተማን ጨምሮ በጊዳ አያና ወረዳ እየተፈፀመ ያለው የንፁኋን እልቂት አድማሱን አስፍቶ በምዕራብ ሸዋ ዞን ስር በኖኖ ወረዳና በአከባቢው እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳና አከባቢው ላይ በቅርቡ መንግስት መር ጭፍጨፋ እንደሚካሄድ ጥቆማዎች እየወጡ ነው።
ለዚህም ደግሞ በአቶ ጃዋር መሀመድ የተመሠረተው ኦኤምኤን/omn/ ሚዲያና ሌሎች የኦሮሞ ፅንፈኛ ኃይሎች ከወዲሁ በአከባቢው አማራዎች ላይ ሀሰተኛ ታርጋ የመለጠፍ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ።
እነዚህ ፅንፈኛ ኃይሎች ከሳምንታት በፊት በወለጋ አማራዎች ላይ የተቀናጀ ሀሰተኛ ታርጋ የመለጠፍ ዘመቻ ሲያካሂዱ የነበረ ሲሆን፡ በቀናት ልዩነት በመከላከያ ሠራዊቱ፣ በክልሉ ልዩ ኃይል፣ በአባ ገዳ ኮማንዶ፣ በረፔ ሎላ፣ በጋቼና ሲርና እንዲሁም በሚኒሻና በእነዚህ ታጣቂዎች ሽፋን የሚሰጣቸው ቆንጨራና ሌሎች ስለታማ መሣሪያዎችን የታጠቁ የቄሮ ቡድን አባላት ጋር በቅንጅት በከፈቱት ዘግናኝ ጭፍጨፋ ከ200 በላይ ንፁኋን ወገኖች ሲገደሉ፡ አሥር የሚደርሱ መንደሮችና ከተማዎች መውደማቸውን መረብ ሚዲያ በተከታታይነት መዘገቡ አይዘነጋም።
ይህ መንግስት መር እልቂት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፡ ቅድመ ጭፍጨፋ የማመቻቸት ስራ ሲሰሩ የነበሩትና በጭፍጨፋው ወቅት የአማራ ተወላጆችን አስከሬን ምስልና ብዛት በመውሰድ "ኦሮሞ ተገደለ" በሚል ለቅሶ በመቀማት እኩይ ሴራ ተሰማርተው የነበሩት እነዚኸው ቆሞ ቀር፣ ወራሪና ጨፍላቂ እንዲሁም ጨፍጫፊ የኦሮሞ ፅንፈኛ ኃይሎች፡ አሁንም በተመሣሣይ በምዕራብ ሸዋ ዞን እና በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ ጭፍጨፋ እንዲካሄድ ቅስቀሳ ጀምረዋል።
የብሔር ግጭት ቀስቃሽና ሀገር አፍራሽ መልዕክቶችን በማስተላለፍና ንፁኋን በገፍ በማስጨፍጨፍ የሚታወቀው አቶ ጃዋር መሀመድ ባቋቋመው ኦኤምኤን ሚዲያና ሌሎች ቆሞ ቀርና ወራሪ እንዲሁም ጨፍላቂና ጨፍጫፊ ፅንፈኛ የኦሮሞ ኃይሎች በተጠቀሱት አከባቢዎች "ኦሮሞ ተገደለ" በሚል በቀጣይ በአማራ ተወላጆች ላይ ለሚፈፀመው ጭፍጨፋ የተቀናጀ ታርጋ የመለጠፍ ዘመቻ መጀመራቸውን መረብ ሚዲያ ተመልክቷል።
ስለሆነው በአከባቢው የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ከወዲሁ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እናሳስባለን።
2September 3, 2026 1.3K