ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ በተከታታይ መነሻውን ከደባርቅ እና ከማይጠብሪ በማድረግ ወደ ዛሪማ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ተንቀሳቅሶ በነበረው የጠላት ብልፅግና ኃይል ላይ በተወሰደ እርምጃ 20 ወታደሮች ሲገደሉ ከ60 በላይ መቁሰላቸው ታወቀ።
በውጊያው ከፋኖ አፈሙዝ ለማምለጥ የእውር ድንብራቸውን ሲሸሹ ከነበሩ የጠላት ኃይሎች መካከል ሰባት ወታደሮች አንድ ብሬንን ጨምሮ ከነሙሉ ትጥቃቸው ዛሪማ ወንዝ ሰጥመው ሕይወታቸው ማለፉን መረብ ሚዲያ ከ3ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል።
በተጋድሎው 15 ክላሽንኮፍ መሣሪያን ጨምሮ ሌሎች የወታደራዊ ቁሳቁሶችና ገዢ ስፍራዎች በፋኖ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

6
1
1September 3, 2026 1.2K