ወገልጤና ከተማን በቁጥጥሩ አድርጎ የነበረው ፋኖ በአሁን ሰዓት ከተማዋን ለቆ ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን በቁጥጥሩ… — Mereja TV — TG.ME

ወገልጤና ከተማን በቁጥጥሩ አድርጎ የነበረው ፋኖ በአሁን ሰዓት ከተማዋን ለቆ ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን በቁጥጥሩ ስር አስገብቷል።

በዚህ መልኩ የሕዝብ ተቋማትን ጠብቆ ያቆየውን ፋኖ ስሙን ለማጥፋት ሲባል መከላከያ ሠራዊቱና የወረዳ ካድሬዎች ተቋማትን እያወደሙ ይገኛሉ።ፋኖ ከተማዋን መልቀቁን ተከትሎ ወደ ከተማዋ የገቡት የብልፅግና መከላከያ ሠራዊት አባላትና የወረዳው ካድሬዎች ፋኖ ጠብቆ ያቆየውን የሕዝብ ተቋም ተራ በተራ እያወደሙ ይገኛሉ።

በርግጥ ፋኖ በከተማዋ በቆየበት ወቅት ምን ያህል የተቋማት ደህንነት እንደተጠበቀ ሕዝቡ ተመልክቷል።

ፋኖ ከተማዋን እንደተቆጣጠረ የወረዳና የከተማ እንዲሁም የቀበሌ አስተዳደር ቢሮዎችን ተጨማሪ 38 ቁልፍ ገዝቶ እስከመቆለፍ የደረሰና ግርግሩን ተጠቅመው የሕዝብ ሀብት የሚያወድሙ ዘራፊና ወንበዴዎች ለመቆጣጠር ሲል ለሊትና ቀን የሚጠብቁ ዋርድያዎች እስከመመደብ የደረሰ አኩሪና ሕዝባዊ ስራ ነው የሰራው።

ወዲያው ፋኖ እንደገባ ግርግሩን ተጠቅመው የተቋማት ኮምፒዎተሮችን ለመዝረፍ ሲሞክሩ የነበሩ ወንበዴዎችን ጭምር እጅ ከፈንጅ በመያዝ የእርምት እርምጃ ወስዷል።

በዚህም የደላንታ ሕዝብ ፋኖ ያደረገውን ጥበቃ ከተመለከተ በኋላ ባደባባይ ወጥቶ ነው ያመሰገነው።

በአሁን ሰዓት ፋኖ ለልዩ ተልዕኮ ከተማዋን ለቆ ወደ ሌሎች ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ማቅናቱን ተከትሎ ወደ ከተማዋ የገቡት የብልፅግና መከላከያ ሠራዊት አባላትና የወረዳው ካድሬዎች የሙስና ወንጀላቸውን ለማጥፋት ሲሉ ሰነዶችን እና ሌሎች ንብረቶችን ካወደሙ በኋላ "ፋኖ አወደመብን" በሚል የስም ማጥፋት ዘመቻ ጀምረዋል።

ወገልጤና ከተማን ተቆጣጥሮ የቆየው ፋኖ ምን ያህል መንግስታዊ ቁመና እንደተላበሰ አስመስክሯል።
❤17
August 31, 2026 2.1K