በአፋብን በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ ንስር በለሳ ክፍለ ጦር ከተውጣጡ የብርጌድ አሀዶች በአመዱት ከተማ በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል ተቀዳጅቷል።
የጠላት ኃይል ከየኋላ ወደ አርባያ ከተማ እንቅስቃሴ ያደረገው ጠላት ላይ ወታደራዊ ገዥ ቦታዎችን በመያዝ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሰውበታል።
የጠላት ኃይል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ወደ መጣበት የኋላ መመለስ እንኳን ሳይችል ቀርቶ ለመፈርጠጥ ተገዷል።
በዚህ አውደ ውጊያ በጠላት ኃይል ላይ በርካታ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ለማድረስ የተቻለ ሲሆን 20 የጠላት ኃይል ሲደመስስ ከ15 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት አስተናግዷል።
ምንጭ፦በአፋብን 3ኛ በላይ ዘለቀ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
1August 28, 2026 1.9K