አፋብን አሳምነው 5ኛ ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር በጠላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ወሰደ!… — Mereja TV — TG.ME

አፋብን አሳምነው 5ኛ ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር በጠላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ወሰደ!

ፀረ-ህዝብ የሆነው ስርዓት ብልፅግና፣ ያደራጀው አድማ ብተና ኃይል በቀን 24/12/2018 ከቀኑ 6፡00 ሰዓት አካባቢ መነሻውን ከአንኮበር ከተማ በማድረግ በፓትሮል ተጭኖ ወደ ቁንዲ በመጓዝ ላይ እያለ፣ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃና የኮሩ ቃኝዎች በቅንጅት ድንገተኛ እርምጃ ወስደውበታል።

ይህ እርምጃ የተወሰደው ልዩ ቦታው ቁንዲ ጊዮርጊስ ላይ ሲሆን ወጤታማ ምት በመሆኑ የጠላት ኃይል መከላከል ሳይችል በርካታ አድማ ብተና ተጎድቷል ሲል የኮሩ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ገልጿል። 

የወገን ኃይል በወሰደው የደፈጣ ጥቃት፣ መቋቋም ያቀተው የጠላት ስብስብ፣ ወደ አንኮበር ከተማ ለመፈርጠጥ ጥረት ቢያደርግም፣ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለጦር የ2ኛ ሻለቃ እና የመሀመድ ቢሆነኝ ኮር ቃኝዎች ልዩ ቦታው አሸዋ መድፊያ አካባቢ መንገዱን ዘግተው በመፈርጠጥ ላይ የነበረውን ጠላት በጨበጣ ውጊያ በርካታ ኃይሉ ላይ መጠነ ሰፊ ርምጃ ተወስዷል። 

በዚሕም የጠላት መመላለሻ የነበረው ፓትሮል መኪና በወገን ጥይት ተመትቶ ከጥቅም ውጪ ሲሆን ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ሙትና በርካታ ቁስለኞች በሌላ መኪና ተጭኖ ወደ መጣበት ከተማ ለመመለስ ተገዷል ሲል አክሎ ገልጿል። 
ምንጭ፦ በአፋብን አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
👍4❤2
August 31, 2026 1.6K