3ኛ, በቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ ከዚህ ቀደም ይታዩ የነበሩ የማስ ሚዲያ አጠቃቀም ችግሮችን በተቀናጀ ሁኔታ በማረምና ድርጅታዊ የሚዲያ አጠቃቀም መርሆችን፣ መመሪያዎችንና ሕግና ደምቦችን ከምንጊዜውም በላቀ ሁኔታ አጠናክረን በመተግበር፣ በድርጅታችን፣ በዕዛችን፣ በማኀበረሰባችን፣ በሰራዊታችንና በአጠቃላይ በትግላችን ላይ ጉዳት ሲያደርሱ የቆዩ ዘ ፈቀዳዊ የሚዲያ አጠቃቀም አሰራሮችን ሸክፈን በተግባር የሚለካ ውጤት ለማምጣት እንደምንሰራ እንገልፃለን። በቀጠናችን፣ ከዕዙ ህዝብ ግንኙነት መምሪያና ከተፈቀደላቸው የሚዲያ፣ ኮሚኒኬሽንና ፕሮፖጋንዳ ክፍል ውጭ የሚደረጉ ኃላፊነት የጎደላቸው የማኀበራዊና የሳተላይት ሚዲያ ያልተገደቡ አጠቃቀሞች በትግላችን ላይ ካላቸው አሉታዊ ተፅዕኖ አኳያ ከዚህ በኋላ የማይደገሙ መሆናቸውን እያሳወቅን፣ ከመምሪያው፣ ሕግና ደንቡ ውጭ ልቅ የሆኑ የሚዲያ አጠቃቀሞች ላይ የሚገኙ የድርጅታችን አመራሮችና አባላት ላይ ተገቢውን ሕጋዊ የእርምት እርምጃ የምንዎስድ መሆኑን ተስማምተናል።
4ኛ, ለትግል እንቅፋት የሆነ፣ ሰራዊታችንን የሚከፋፍልና ማኀበረሰባችንን ላልተገባ ወጭና እንግልት የሚዳርግ ዘፈቀዳዊ የፋይናንስ አሰባሰብ፣ ቁጥጥርና ትግበራ በተቀናጀ ሁኔታ በዕዛችን ተስተካክሎ ለቀጣይ በድርጅታችን ፋይናንስ መምሪያና ሕግ ብቻ ተፈፃሚ ሆኖ እንዲቀጥልና ጥብቅ የኦዲትና ቁጥጥር ስራዎች ከተጠያቂነት ጋራ እንዲኖሩ ዕዛችን ይሰራል።
5ኛ, የድርጅታችንን ዓላማ ከግብ ለማድረስና ሰፊው የአማራ ህዝብ በኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ የተጋረጠብንን ሁለንተናዊ የህልውና አደጋ ለመመከት የምናካሄደውን ፖለቲካዊ የትጥቅ ትግል ከድርጅታዊ መርህና መመሪያ ጋራ አቀናጅተን በተዋረድ ቀጠናችንን፣ ማኀበረሰባችንንና ሰራዊታችንን በሚመጥን መልኩ እንሰራለን። ከሌሎች ዕዞችም ጋራ ከዚህ ቀደም የነበረውን ግንኙነት ወደ ከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ በተቀናጀ ሁኔታ እንሰራለን።
6ኛ,የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ፤ ሊቀመንበር የነበሩትን አርበኛ ዘመነ ካሴን ጨምሮ፣ በድርጅት ኃላፊነት ወደ አፋብን የሄዱ በምክተል ሊ/መንበርነትና የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊነት፣ በምክትል ሊ/መንበርነትና ወታዳራዊ አዛዥነት እንዲሁም በየመምሪያ ኃላፊነት የቆዩ ስራ አስፈፃሚ አባላትና የትግል ጓዶቻችን በቀጠናችን በአመራርነት በነበሩበት ወቅት ላበረከቱት ከፍተኛ የትግል አስተዋፅኦ፣ የቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ አዲሱ የስራ አስፈፃሚ አባላት ከልብ አመስግነው በቀጣይ የጀመሯቸውን መልካም ስራዎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል።
አፋብን፤ ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ፣ አዲሱ የስራ አስፈፃሚ አባላት ላለፉት ተከታታይ ቀናት በአካል በመገናኘት ባካሄድው ጥብቅ ድርጅታዊ ውይይት ከ13 በላይ አጀንዳዎችን በመለየት አቅርቧል። በሰከነና በሰለጠነ ጓዳዊ መንፈስ ውይይቱን ያካሄደው ዕዛችን፣ ከዚህ ቀደም የነበሩ ዘፈቀዳዊ አሰራሮች በማረምና በማስተካከል፣ ድርጅታዊ መርህና አሰራር ላይ ተመርኩዞ በየደረጃው የማኀበረሰባችንንና የሰራዊታችንን ሰፊ ጥያቄዎች ለመመለስ በፍፁም ጓዳዊ ዝምድና፣ በታደሰ የትግል መንፈስና ጥንካሬ ከዚህ ቀደም የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን በተግባር ለይቶ በማስቀረት ታጋዩንና ህዝቡን ለመካስ በከፍተኛ ወኔና ፍላጎት ላይ ይገኛል። በመሆኑም በተዋረድ የዚህን ጥልቅ ውይይት ዉሳኔ በጉጉት ስትጠባበቁ የነበራችሁ የዕዝ፣ የኮር፣ የክፍለጦርና የሻለቃ አመራሮቻችንና ማኀበረሰባችን የዚህ መልካም መንፈስ አጋር እንድትሆኑ በታላቅ አክብሮት እናሳስባለን።
ነሐሴ/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፤ ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ፤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!
ቴሌግራም ገፃችን👉https://t.me/MerebMedia24