በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የጦር አውሮፕላኖች ሳምንታዊ የጦር መሣሪያ ማራገፍ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸው… — Yeju Times-የጁ — TG.ME

በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የጦር አውሮፕላኖች ሳምንታዊ የጦር መሣሪያ ማራገፍ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸው ተገለጸ!

በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በየሳምንቱ የጦር አውሮፕላኖች በስፋት የጦር መሣሪያዎችን በማጓጓዝ ላይ እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል።

የሲቪል በረራዎችን እንቅስቃሴ ሽፋን በማድረግ በሳምንት ለሁለት ቀናት ያህል ያለማቋረጥ የጦር አውሮፕላኖች ወደ ኤርፖርቱ በማሳረፍ ከባድና ቀላል የጦር መሣሪያዎችን ማራገፍ ተጀምሯል። ለዚሁ የመሣሪያ ማጓጓዝ አገልግልት እየዋሉ ከሚገኙት መካከል «ኢሉሺን ኢል-76» (Ilyushin Il-76) የተባለ የሩሲያ/ሶቪየት ሕብረት ምርት የሆነ ከባድ የጭነት አውሮፕላን እንደሚገኝበት ታውቋል።

ይኸው ያልተቋረጠ የመሣሪያ ማጓጓዝ እንቅስቃሴ በአሁኑ ወቅት በአቪዬሽንና በኤርፖርት አካባቢ ባሉ የደህንነት አካላት ዘንድ በሰፊው የሚታወቅ እንደሆነ ተነግሯል።

አገዛዙ በሀገሪቱ ልዩ ልዩ አካባቢዎች እየደረሰበት ያለውን ወታደራዊ ሽንፈት ለማካካስና የጨበጣ ውጊያዎችን ለመቋቋም በሚል እያካሄደ ያለው ይህ የመሣሪያ ዝውውር፣ የአቪዬሽን ደህንነት ደንቦችን የሚጥስና የሲቪል በረራዎችን ለከፍተኛ አደጋ የሚያጋልጥ ተግባር እንደሆነ ተጠቅሷል።
©ኢትዮ 251 ሚዲያ

የመረብ ሚዲያ ቴሌግራም ገፅን ይቀላቀሉ👉
https://t.me/MerebMedia24
https://t.me/MerebMedia24
https://t.me/MerebMedia24
September 4, 2026 22