በህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መካከል የመፈንቅለ መንግስት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተሰማ በአሁኑ ወቅት… — Mehal media — TG.ME

በህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መካከል የመፈንቅለ መንግስት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተሰማ

በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ፖለቲካዊና ህልውናዊ ኪሳራ ውስጥ የሚገኘው የህወሓት ቡድን፡ በውስጡ በተፈጠረ ከፍተኛ ውጥረት ምክንያት በወታደራዊ አመራሮቹ መካከል የመፈንቅለ መንግስት ሴራ እየተጠነሰሰበት እንደሚገኝ ምንጮች ጠቆሙ።

እንደ ምንጮቹ ገለጻ፡ በህወሓት የፖለቲካ ክንፍ አመራሮች ዘንድ መገለልና ዘመናዊ መዋከብ እየደረሰባቸው ያሉት የቡድኑ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች (ጀነራሎች)፡ አሁን ባለው የትግራይ ክልል ህገወጥ አስተዳደር ላይ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ ስልጣን ለመቆጣጠር በድብቅ መምከር ጀምረዋል።

ህወሓት በሁሉም አቅጣጫ ገጥሞታል ከተባለው ሁለንተናዊ ውድቀትና የፖለቲካ ኪሳራ ለማንሰራራት አለመቻሉ ለዚህ ውሳኔ ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተመልክቷል።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙት የህወሓት የፖለቲካ ባለስልጣናት በአሁኑ ወቅት በገዛ ጥላቻቸውና በውስጥ ክፍፍሉ ምክንያት በከፍተኛ ፍርሃትና ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል።
❤35👍15👏9
September 3, 2026 2.6K 1