ለሻቢያው አጋፋሪ እና የህወሓት ቃል አቀባይ ስታሊን፤ የተሰጠ የ"ክላሽ እና የድሽቃ" ማብራሪያ ሰሞኑን ሚዲያ… — Mehal media — TG.ME

ለሻቢያው አጋፋሪ እና የህወሓት ቃል አቀባይ ስታሊን፤ የተሰጠ የ"ክላሽ እና የድሽቃ" ማብራሪያ
ሰሞኑን ሚዲያ ላይ ገምዳላ እውነቶችን እያወጣሁ ራቁታችሁን ሳስቀራችሁ፣ መሸሸጊያ ሲጠፋችሁና የምትመልሱት አመክንዮ ሲያልቅባችሁ፣ እንደለመዳችሁት ወደ ብሄር ስድብና ትምክህት መውረዳችሁን አይቼዋለሁ። በተለይ አንተ ስታሊን፣ እኔን ለማንጓጠጥ ብለህ ክቡር የሆነውን የሀዲያን ህዝብ እና የኢትዮጵያን የቁርጥ ቀን ጀግና ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስን ለማንቋሸሽ የሞከርከው ሙከራ፣ ከድንቁርናህ ማማ ላይ ሆነህ የራስህን ውድቀት ያወጅክበት ትልቅ ኮሜዲ ነው።
"የሀዲያ ህዝብ የታንክ፣ የክላሽ፣ የስናይፐር እና የድሽቃ ድምጽ ለይቶ አያውቅም፤ የትግራይ እና የኤርትራ ህዝብ ግን የመረረው ስለሆነ የጥይት ድምጽ በደንብ ያውቃል" ብለህ ስትዘባርቅ ሰምቼሃለሁ። እውነት ለመናገር በዚህ ሎጂክህ በጣም ነው ያሳቅኸኝ! ለካ ህዝብን ማስተማር፣ ማልማት፣ በሰላም ማኖር ትታችሁ፣ ትውልድን የጦርነት ማገዶ ማድረጋችሁ፣ ህፃናትን የጥይት ድምጽ እያስቆጠራችሁ ማሳደጋችሁ እንደ ትልቅ ስልጣኔና "የጀግንነት ፒኤችዲ" ሆኖ ነው የምትኮሩበት? የሀዲያ ህዝብ የጥይትና የመድፍ ድምጽ በየቀኑ መስማት ያልፈለገው ፈሪ ስለሆነ ሳይሆን፣ አእምሮው ከጥፋት ይልቅ ለልማት፣ ከመግደል ይልቅ ሀገር ለመገንባት የነቃ የሰለጠነ ህዝብ ስለሆነ ነው።
የሀዲያ ህዝብ የክላሽ ድምጽ ላያውቅ ይችላል፤ ነገር ግን እናንተን በየጉድጓዱ አይጥ ያስመሰሉ፣ ሰማዩን ምድር ያደረጉባችሁ እንደ ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ያሉ የሰማይ ላይ ንስሮችን እና የጦር ጠበብቶችን አምጦ የወለደ ጀግና ህዝብ ነው። ስታሊን፣ የኮሎኔል በዛብህ ስም ሲነሳ ዛሬም ድረስ ሻቢያዎች በየተኛችሁበት ብርድ ብርድ የሚላችሁ፣ በዛብህ ማለት ገና ሞተሩን ሲያስነሳ አስመራ ላይ ሱሪያችሁን የሚያስርጥባችሁ የእሳት ነበልባል ስለነበር ነው።
በዛብህ ጴጥሮስ ኤርትራ ምድር የሄደው ለሽርሽር አልነበረም፤ ጀግንነትም አምሮት አይደለም። እናንተ በጭካኔና በአውሬነት የትግራይ ህፃናትን በአይደር ትምህርት ቤት በጄት ደብድባችሁ ደማቸውን ስታፈሱ፣ ያንን የንፁሃን ህፃናት ደም ለመበቀል፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር በጀግንነት የተሰለፈ የሀዲያ አንበሳ ነው። ዛሬ እናንተ ስለ እሱ ለማውራት ሞራሉም፣ ታሪኩም፣ ቁመናውም የላችሁም። በዛብህ ማለት የኢትዮጵያ ሰራዊት አብነት፣ የሀዲያ ህዝብ ኩራት እና የኢትዮጵያ ህዝብ የልብ ትርታ ነው!
እናንተ "በሂማን ዌቭ" (Human Wave) ምስኪኑን ወጣት እያስጨረሳችሁ፣ በሬሳ ላይ እየተረማመዳችሁ ስልጣን ለመያዝ የምታልሙ የፖለቲካ ነጋዴዎች ናችሁ። እኔ ደግሞ ይሄንን ፀረ-ህዝብ እና ፀረ-ኢትዮጵያ ሴራችሁን እያጋለጥኩ፣ እውነትን በማስረጃ እያቀረብኩ ማስጨነቄን እቀጥላለሁ። የሀዲያን ህዝብ፣ የኢትዮጵያን ሰራዊት እና ኮሎኔል በዛብህን ለመተቸት መሞከር የዝንብን ዝሆን የመግፋት ከንቱ ልፋት ነው። ወደዳችሁም ጠላችሁም፣ እውነቱ እናንተን መግረፉን አያቆምም፤ እኔም የሀሰት ትርክታችሁን ከመሰባበር ወደ ኋላ አልልም!
❤21👏8🙏7🏆1
September 3, 2026 2.3K 1