የዚህን ወንድማችንን የተቆራረጡ ቪድዮዎች በገፄ ላይ ሲመጡ አዳምጫቸው ነበር።
ታሪኩ ልብ ይሰብራል፣ በርካታ የዱንያ ሙሲባዎችን ያሳለፈ ብርቱ ሰለምቴ ወንድማችን ነው።
አሁንም ላይ የሚሠራው ሊስትሮ ነው። በጣም ያሳዘነኝና ልቤን የነካው ንግግሩ፤ ሰዎች እኔን ጫማ አያስጠርጉኝም። ትልቅ ሰው ነው በሚል እርሱን ወደታች ጫማቸውም ማስጠረግ ኃፍረትና ሼም ሆኖባቸው ነው። በርግጥ አልፈርድባቸውም። «ለኔ የሚጠቅመኝ ግን ቢያስጠርጉኝ ነበር!» ሲል የበለጠ ልቤን ነካው።
እኔም ቢሆን ብሆን ይህ ወንድማችን ቢያጋጥመኝ፤ ደፍሬ በዚህ ሐይባው ለማስጠረግ ይከብደኛል። ግን ደግሞ ለርሱ የሚጠቅመው ባስጠርገው ነው።
አላህን በማይፈሩ የምድር ጭራቆች፣ የሰው ሸይጧኖች ዘግናኝና ለጆሮ ሰቅጣጭ ግፍ የተፈጸመበት፣ 4 ልጆቹን በተከታታይ በሞት ያጣ… ወንድማችን ነውና፤ ሚዲያ ላይ ከወጣ አይቀር፤ ላልሰማችሁ ቪድዮዎቹን እያጋራኋችሁ፤ እንደተለመደውና ለሌሎች እንደምናደርገው፤ ዛሬም ለዚህ ወንድማችን 3 ነገሮችን ተረባርበን ብናደርግ ብዬ አሰብኩ።
1) ከሊስትሮው የተሻለ ገቢ የሚያገኝበትንና ኑሮውን መምራት የሚያስችለውን መካከለኛ አዋጭ ቢዝነስ ብናስጀምረው፣
2) ከቢዝነሱ ማቋቋሚያ የተወሰነ እንዲተርፈው አድርገን፤ ስነ ልቦናውም ስለተጎዳ፤ ዑምራ ብናስደርገውና መንገሱን አዲሶ ቢመጣ ብዬ አሰብኩ።
3) የጤና ተቋም ያላችሁ አካላት፤ አናግሩኝና በአካል ተገኝቶ የተለያዩ ምርመራዎችንና የስነ ልቦና ጥገና ትሪትመንቶችን ብታደርጉለት መልካም ነው።
በዚህ ረገድ ፈቃደኛ የሆናችሁ፤ ሃሳባችሁን ልስማና ለድጋፉ በራሱ ስም የተከፈተ አካውንት አጋራችኋለሁ። የወንድማችን ስሙ ዑመር ታረቀ ነው።
እስኪ ቪድዮውን አጋጥሟችሁ የሰማችሁት ካላችሁ፤ ሃሳባችሁን አካፍሉኝ።
||
t.me/MuradTadesse
Forwarded fromMurad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

3August 12, 2026 349