ሀከር ምንድን ነዉ ? | Who is a Hacker ሀከር ማለት አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን አንድን ኮምፒዉተር… — 💻ᴍᴀᴍ ᴛᴇᴄʜ ᴛᴇᴄʜɴᴏʟᴏɢʏ ɪɴsᴛɪᴛᴜᴛᴇ📲 — TG.ME

💻ᴍᴀᴍ ᴛᴇᴄʜ ᴛᴇᴄʜɴᴏʟᴏɢʏ ɪɴsᴛɪᴛᴜᴛᴇ📲Photo
ሀከር ምንድን ነዉ ? | Who is a Hacker
ሀከር ማለት አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን አንድን ኮምፒዉተር ወይም የኮምፒዉተር ኔትወርክ ለራሱ ትርፍ ወይም ለመዝናናት ሰብሮ የሚገባ ነዉ።
የሀከር አይነቶች | Types of Hackers
ሀከሮች በሶስት ወሳኝ አይነቶች ይከፈላሉ :-
White Hat Hackers :- እነዚህ ሀከሮች የሀኪንግ እዉቀታቸዉን ተጠቅመዉ ህገወጥ የመረጃ ብርበራ የማያደርጉ ናቸዉ ስለዚህ ጥሩ ሀከሮች ነዉ የሚባሉት እንዲሁም Security expert በመባል ይታወቃሉ።
Black Hat Hackers :- የነዚህ አይነት ሀከሮች ብዙ ጊዜ crackers ይባላሉ እነዚህ ሀከሮች የሀኪንግ እዉቀታቸዉን ተጠቅመዉ ህገወጥ ተግባራትን ያከናዉናሉ ለምሳሌ ልክ እነደ credit card ዘረፋ ባንኮችን ሀክ ማድረግ ወዘተ ክሬዲት ካርድ ዘረፋ ላይ የሚሳተፉ ሀከሮች ካርደር ይባላሉ ሌላ ጊዜ በሰፊዉ እንቃኛቸዋለን።
Grey Hat Hackers :- ግሬይ ሀት የምንላቸዉ በwhite hat እና በblack hat መካከል የሚገኙ hybrid ናቸዉ ይህም ማለት አንዳንዴ black hat አንዳነዴ ደሞ white hat ሀከርስ ይወላዉላሉ ማለት ነዉ
የሀከሮች ደረጃ | Hacker Hierarchy
Scriptkiddies :- እነዚህ የሀኪንግ ልምድ የሌላቸዉ ግለሰቦች / ቡድን ግን ሀከር መሆን የሚፈልጉ ናቸዉ ሀክ ለማድረግ የሚጠቀሙትም ready made tool ወይም የተዘጋጀ ሶፍትዌር ነዉ በዙ ጊዜም ልምድ ስለሌላቸዉ እራሳቸዉን harm ያደርጋሉ አንድ ታዋቂ ጥቅስ አለ "Little knowledge is dangerous" ይህም ብዙ ጊዜ የምናየዉ ችግር ነዉ።
Intermediate hackers :- ከscriptkiddies የበለጠ የሀኪንግ ልምድ እንዲሁም እዉቀት ያላቸዉ ሀከሮች ናቸዉ ግን የራሳቸዉን exploit ወይም የሀኪንግ ሶፍትዌር መስራት አይችሉም ቢሆንም ጥሩ ልምድ ያላቸዉ ሀከሮች ናቸዉ።
Professional or Elite hackers :- እነዚህ ልምድ ያላቸዉ ሀከሮች የራሳቸዉን exploit ወይም የሀኪንግ ሶፍትዌር መስራት ይችላሉ ስለሆነም የትኛዉም አይነት system ሰብረዉ መግባትና ራሳቸዉን የመደበቅ ልምድ አላቸዉ።


ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
#ፔጄን_like_share_ያድርጉ_መረጃ_እንዲደርሳችሁ👍


https://t.me/mamtech1
Telegram
💻ᴍᴀᴍ ᴛᴇᴄʜ ᴛᴇᴄʜɴᴏʟᴏɢʏ ɪɴsᴛɪᴛᴜᴛᴇ📲
እንኳን ወደ M A M T E C H በሰላም መጡ ። በዚህ ቻናል 🌎 ስለ ቴክኖሎጂ የተሟላ መረጃ የሚያገኙበት: 🕌 በተጨማሪም ወቅታዊ ኢስላማዊ መረጃወችና ኢስላማዊ ትምህረቶችን የሚያገኙበት ቻናል ነው። ➡ ማንኛውም አስተያዬት ሲኖሮዎት 👇👇 @Mam_tech_1_bot
👍1
August 30, 2026 88 1