zakiphi @zakiphi @zakiphi #"አን ዱ " የለም እንጂ " አን ዱ"ማ ብኖር #ስንቱን እንደገና…

@zakiphi
@zakiphi
@zakiphi



#"አን ዱ " የለም እንጂ " አን ዱ"ማ ብኖር
#ስንቱን እንደገና እንፈጥረው ነበር !!!!

#"አን ዱ" ብዙዎቻችን በኮምፒውተር ላይ #Undo("አን ዱ")ን እናውቃለን።

ገጣሚውም የህንን አይቶ ይመስለኛል ግጥሙን ያለው።


እውነትም እንደ ኮምፒውተር ሁሉ በኑሯችንም ውስጥ ብኖር ምናለበት

ከእውቀት ይበልጥ ጥላቻና ዱላ ያስተማሩንን መምህራን "አን ዱ" ብለን እንዲያስተምሩን ሌላ እድል በሰጠናቸው።


💟💟 ትናንት ላይ ያስቀየምናቸውን " አን ዱ" ብለን ስተታችንን ማስተካከል በቻልን።

✅✅ዛሬ ላይ በጎጥና በዘር እንድንከፋፈል ምክንያት የሆኑትን ነገሮች "አን ዱ" ማድረግ በቻልን።

🔰🔰 ሃገር መምራት ሳይኖሮባቸው ሃገር የመሩትን ሞት ሳይገባቸው የሞቱትን ምነው "አን ዱ" በልናቸው።


#"የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም" ይላል የሃገሬ ሰው። ሰውየው መንገድ ሲሄድ ዝናብ ይደርስበትና ሊጠለል ሰው ቤት ገባ። የተቀበሉት ሰዎች እራት እየበሉ ስለነበር " እባክህ ብላ" ብለው ለመኑት።እርሱግን ዝናቡ ሲያባራ ቤቴ ደርሼ እበላለው ብሎ "አይ በልቻለው በቃኝ" አላቸው። እነርሱም እራታቸውን በሉ። ዝናቡ አላባራ አለና እዛው ማደር ግድ ሆነበት። ፆሙን አደረ። በንጋታው ቤቱ ሲገባ "እንዴት አደርክ" ብለው ጠየቁት።
እርሱም "አፌን ወለም ብሎኝ ፆሜን አደርኩ" አላቸው።


ህይውት "አን ዱ የላትም ከመወሰናችን በፊት ቆም ብለን ማሰብ ያስፈልጋል።

ፍንጭ፡ ዳንኤል ክብረት የሁለት ሐውልቶች ወግና ሌሎችም



🔊🔊ገንቢ ለአስታየት እና ጥያቄዎቻችውን @zakimg ያድርሱን🀄️🀄️🀄️



@ewuketmad
October 27, 2026 427