አህያው በአጋጣሚ የአንበሳ ቆዳ ያገኝና ይለብሰዋል። "ዛሬማ ማንም አያቀልለኝም!" ብሎ ወደ ቀበሮዎች መንጋ… — 🖤 قرة عين 🖤 — TG.ME

አህያው በአጋጣሚ የአንበሳ ቆዳ ያገኝና ይለብሰዋል። "ዛሬማ ማንም አያቀልለኝም!" ብሎ ወደ ቀበሮዎች መንጋ ሲገባ...ቀበሮዎቹ "አንበሳ መጣብን!" ብለው በድንጋጤ እግሬ አውጪኝ ይላሉ።
....
አህያው በነገሩ እየተገረመና በደስታ እየፈነጠዘ ወደ ሜዳ አህያዎች ያመራል፤ እነሱም በፍርሃት ተበታተኑ። ቀጥሎ "እስኪ ጉዳቸውን ልይ!" ብሎ ወደ ጅቦች መንጋ አመራ። ጅቦቹም በፍርሃት እየጮሁ መሸሽ ጀመሩ።
...
አህያው በደስታ ብዛት ግራ ተጋባ፤ በቃ የደስታውን ጥግ ለማሳየት "አንዴ ልጩህ" ብሎ ማናፋት ጀመረ። በዚህ ጊዜ ጅቦቹ ድምፁን ሰሙት... "ኧረ ይኸ ነገር አህያ ነው!" ብለው ተመልሰው ቦተረፉት ።
....
እውነተኛ ማንነት የሚገለጠው ሰው ሁሉንም ነገር በእጁ አስገብቻለሁ ብሎ ባወራ ጊዜ ነው። አፍ ሲከፈት ውስጥ ይታያል አይደል የሚባለው? በሱፍ የተደበቀ ሌባ፤ በፀዓዳ ነጭ ስር የተደበቀ እድፍ፣ በለስላሳ ምላስ ስር የተደበቀ እኩይ ልብ አለ። ጊዜ ደግሞ ይገልጣል። ብንችል ራስን መሆን ውብ ነው።

ማዕደ ጥበብ
©️የነቢያት ፋና
❤1🥰1
August 2, 2026 357 1