ማን እንዳንተ! 😶‍🌫️ በቅርቡ ለረጅም ጊዜ በካንሰር ህመም ሲሠቃይ ቆይቶ ወደ አኺራ የሄደ እንዲሁም አብሮ… — 🖤 قرة عين 🖤 — TG.ME

ማን እንዳንተ! 😶‍🌫️

በቅርቡ ለረጅም ጊዜ በካንሰር ህመም ሲሠቃይ ቆይቶ ወደ አኺራ የሄደ እንዲሁም አብሮ አደግ ጓደኛዬ ነበር ። ብዙ አቅም ያለው፤ ገና ብዙ ይሠራል ተብሎ የሚጠበቅ ነበር ። ግና ማንም ሮጦ የማይቀድመው ሞት ቀደመው 💀፣ ማንም ገላግሎት የማይጥለው ሞት ጣለው ፡፡ እላህ አብዝቶ ይዘንለት። 🤲 እኛም እሱ ወደሄደበት ዓለም የሄድን ቀን በእዝነቱ ያስበን ። በረሕመቱ ያካብበን ።

የዚህ ወጣት የመጨረሻ ኑዛዜው ትኩረት የሚስብና ለማስተንተን የሚያነሳሳ ነው። 📜 እንዲህ ብሎ ነበር ።

“የሞትኩ እንደሆነ 'አምላክ' ወይም 'ፈጣሪ' በሚለው ሥም ዱዓ እንዳታደርጉልኝ። 🙅‍♂️ አላህ አምላክ እና ፈጣሪ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን ። አዎ እሱ ፈጣሪያችንና አምላካች ነው ። “አር-ረህማን” /አዛኝ/ በሚለው ሥሙ ዱዓ አድርጉልኝ 📿:: የዘውትር እዝነቱ አይለየኝ ዘንድ ።”

በርግጥም የሚገርም አባባል ነው የሆነብኝ ። አምላከ ፈጣሪ ሆይ! ብለን ዱዓ ብናድርግለት ችግር እንደሌለው እሱም እኛም እናውቃለን 🤝 ። ግና የፈጣሪውን አምላከ እዝነቱን አብዝቶ አሰበ ። እዝነቱም ያዝንለት ዘንድ ተመኘ ። ፈጣሪያችን፣ አምላካችን፣ ጌታችን፣ አላህ፣ አዛኝ፣ ሩህሩሁ ጌታ... ብዝቶ ይዝንለት፣ የመቃብር ህይወቱን ያብራለት 💡፣ ወደ ጀነት መንገድም ያግካለት ። እኛም እሱ ወደሄደበት ተጓዦች ነንና ዛሬም ነገም የአላህ እዝነት አይለየን 🤲


ከአላህ ጋር 📚
❤3
July 20, 2026 408 1