ምን ብትወደኝ ነው ♡ ምን ብትወደኝ ነው ምን ብታስበኝ አዲስ ዘመንን ቀን ያሳየኸኝ ኦ አምላኬ ዘመንን ካየሁ… — ኩራዝ — TG.ME

♡ ምን ብትወደኝ ነው ♡

ምን ብትወደኝ ነው ምን ብታስበኝ
አዲስ ዘመንን ቀን ያሳየኸኝ
ኦ አምላኬ ዘመንን ካየሁ ከተሻገርኩኝ
ኦ ጌታዬ እዘምራለሁ ስቡህ እያልኩኝ(፪)

ጠዋትም የለኝ ካንተ በቀር ማለዳዬ ነህ
ማምሻዬም አንተ አልሻገርም አንተ ካልፈቀድህ
ማዕበል ወጀቡን አሳልፈህ ጨለማውን አብርተህ
በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና(፪)     
አዝ= = = = =

አልፍ እንድትሆን አንተ የባረካት ከመሬት ወድቃ
ትላንትናዬን ወዜን ባርከኸው ለዚህ ብበቃ
ባጌጠችው የምድር መሀል ሆኜ እቀኛለሁ ስለአዳኜ
በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና(፪)        
አዝ= = = = =

ፍሬ ፈልገህ መጣህ ወደኔ በብርሀን ጸዳል
ፀሐይ አውጥተህ ልትባርከው ጌታ ፈቅደሀል
ያንተ ወንዞች ውሃ ከተሞሉ
ተራራዎችም ምስጋናህን ያመጣሉ
በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና(፪)       
አዝ= = = = =

ማለፍ በክንድህ አዲስ ዘመንን ላንተ መዋጀት
ግዛው ዘመኔን ውረስ አምላኬ የኔን ማንነት
አዝማናቱ ስራህን እያሳየ ልሁንልህ ከዓለም የተለየ
በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና(፪)        
አዝ= = = = =

ቀንን ብቆጥር ዘመን ባሰላ ካልተለወጥኩኝ
ከጸጋህ ዙፋን በዕምነት ቀርቤ ካልተፈወስኩኝ
ምን ሊረባኝ ካንተ ጋር ካላረጀሁ
ያለቃልህ በዘመን እንዲያው ባውጀው
በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና(፪)

✞ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
ምን ብትወደኝ ነው
September 5, 2026 170 1