LAFTO W0REDA 06 COMMUNICATION-LAFETO 6 CHANNEL: post #1143 — TG.ME

በወረዳ ማዕከል ጥናትና (LDP) ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ዘመናዊና ስማርት ለማድረግ በተዘጋጀው ጥናት (LDP) ዙሪያ ከብሎክ ከተውጣጡ ብሎክ ኮሚቴዎችና ነዋሪዎች ጋር ውይይት ተደረገ።

መድረኩን የመሩት የክፍለ ከተማው ፕላና ልማትሽፅ/ቤት የስፔሻል ፕላን ዝግጅት ቡድን መሪ ወ/ሮ ኡርጂ ወንድሙና የማህበራዊ ኢኮኖሚ ፕላን ባለሙያ አቶ ስንታየሁ ገ/ዮሃንስ ሲሆን የወረዳ ማዕከላትን ዘመናዊና ስማርት ለማድረግ የተጠናውን ጥናት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

ጥናቱን ለውይይት የቀረበው ህዝቡ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ህብረተሰቡ በልማቱ ተሳታፊና አጋዥ እንዲሆን ታስቦ መሆኑ ከመድረኩ የተገለጸ ሲሆን በውይይቱ የሚነሱ ሃሳብና አስተያየቶችን በቀጣይ ለማካተት የሚያግዝ አስተያየቶች ተነስተዋል።

#01_11_20181ዓም
July 8, 2026 98