LAFTO W0REDA 06 COMMUNICATION-LAFETO 6 CHANNEL: post #1135 — TG.ME

ከተጀመረ አራት አመታትን ያስቆጠረውና ስራው ተቋርጦ የነበረው ከመብራት ሃይል ቬነስ ህንጻ እስከ ጎፋ ካምፕ ያለው የመንገድ ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ እየተጠናቀቀ መሆኑእንዳስደሰታቸው ነዋሪዎች ገለጹ

በባጃጅ ማሽከርከር ስራ ላይ የተሰማራው ወጣት ወንደሰን ተመስገን "መንገዱ ተጀምሮ ለአመታት የተቋረጠ በመሆኑ ለባጃጅ ስራው ሆነ ለነዋሪዎች አስቸጋሪ ነበር ብሏል ። በቅርቡ ስራው ሲጀመር እንዲህ በአጭር ጊዜ ስራው ይጠናቀቃል ብየ አላሰብኩም ያለው ወጣቱ መንገዱ እንዲህ አምሮ በፍጥነት በመሰራቱ ሰርተን ለጥገና ስናውለው የነበረውን ወጭ አስቀርቶልናል ብላሏል
በሸቀጣሸቀጥ ስራ ተደራጅተው ሲሰሩ ያገኘናቸው ወ/ሮ የሺ ከበደ "መንገዱ ቀደም ብሎ ለገበያ ምቹ ባለመሆኑ ለኛም ለሸማቹም አስቸጋሪ ነበር በአሁኑ ወቅት ግን አስፋልቱ በአጭር ጊዜ ተነጥፎ በመጠናቀቁ ከአቧራና ከጭቃ ተላቀናል በጣም ደስ ብሎኛል ሲሉ ለወረዳው ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ገልጸዋል ።

በአድዋ ፩ ደረጃ ትም/ቤት ሰራተኛና ጎፋ ካምፕ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ቀለሟ ግዛው " ይህ መንገድ ተጀምሮ ላለፉት አራት አመታት ስራው ቆሞ ነበር ። በዚህም ህብረተሰቡ ለበርካታ አመታት ጥያቄ ሲያነሳ የነበረና ለአስተዳደሩ ጥያቄ ስናቀርብበት የነበረ ሲሆን መንግስት ይህን የመልካም አስተዳደር ችግር በመገንዘብ ለሶስት ወር በማይሟላ ጊዜ መንገዱን እንዲህ ባመረና ደረጃው በጠበቅ መልኩ ማጠናቀቁ የሚደነቅ፣ ሊያስመሰግነው የሚገባ ስራ ነው ብለዋል ። መንገዱ በመጠናቀቁ ከስራ ቦታ ቤታቸው በእግራቸው በመጓዝ በቀላሉ እንደሚደርሱ የገለጹት ወ/ሮ ቀለሟ የእግረኛ መንገዶችን በተጀመረው ፍጥነት እንደሚጠናቀቅም በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ ሲሉ ለወረዳው ኮሙኒኬሽን ፅ
👍3
March 24, 2026 158