በአገግልግሎት አሰጣጥ ላይ መሻሻል መኖሩን ተገልጋዮች ገለጹ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ መሻሻል መኖሩን ተገልጋዮች ገለጹ ።
የወረዳ 06 ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት በዛሬው እለት ምልከታ ያደረገ ሲሆን በናአገግልግሎት አሰጣጥ ያለበት ደረጃ በተመለከተ ተገልጋዮችን አነጋግሯል።
በወረዳው ሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገግሎት ፅ/ቤት መታወቂያ ለማደስ እንደመጣ የገለጸልን አቶ ሽመልስ ሌሊሴ "በዚህ ፅ/ቤት ቀደም ብሎ የነበረው የአገጋልግሎት አሰጣጥ ሲስተም የለም ፣ መብራት ጠፋ በሚል ምክንያትና እንግልት የሚበዛበት ነበር በዛሬው እለት ግን ከሰራተኞች አቀባበል ጀምሮ በጣም ጥሩ ነው ። የፈለኩትን አገልግሎትም በፍጥነት አግኝቻለሁ ሲሉ መሻሻል መኖሩን ገልጸዋል።
በወረዳው ስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሲገለገሉ ያገኘናቸው አቶ ፍስሃየ ገ/እግዚአብሄር " እኔ የመጣሁት የስራ እድል እንዲፈጠርልኝ ለመጠየቅ ሲሆን ከሃላፊ ጀምሮ እስከ ሰራተኞች የሚያስተናግዱበት መንገድ በጣም ጥሩ፣ በትህትና በመሆኑ ከሚወራው በተቃራኒ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ።" ብለዋል ። ተገልጋዩ ተራው እስኪደርሰው የሚጠብቅበት ምቹ ቦታና ወንበር መኖሩንም አቶ ፍስሃየ ጨምረው ገልጸዋል
#ንፋስ_ስልክ_ላፍቶ_ወረዳ_06_ኮሙኒኬሽን
09/07/2018

March 21, 2026 143