በቅዳሜና እሁድ ገበያ በመሸመታቸው የኑሮ ውድነት ጫናን መቀነስ መቻላቸውን ሸማቶች ገለጹ
በቅዳሜና እሁድ ገበያ ማእከላት የተለያዩ ምርተችን በመሸመታቸው የኑሮ ውድነት ጫናን መቀነስ መቻላቸውን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማን ወረዳ 06 ጎፋ ካምፕ በሚገኘው ማእከል ሲገበዩ ያገኘናቸው ሸማቶች ገለጹ።
የወረዳው ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት በዛሬው እለት በገበያ ማእከሉ በመገኘት በምርት አቅርቦት፣ ጥራትና ዋጋ ዙሪያ ሸማቶችን አነጋግሯል።
በጎፋ መብራት ሃይል ኮንዶምንየም ነዋሪ የሆኑትና ብዙ ጊዜ ግብይት የሚፈፅሙት በዚህ መሆን የገለጹልን ወ/ሮ ሄለን አንዷለም " በገበያ ማእከል የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ከውጭ ነጋዴው 20- ከ25 ብር በቀነሰ ዋጋ የሚሸጥ በመሆኑ ኑሮየን እየደገፈልኝ ነው ። ቦታውም ከመኖሪያ አካባቢየ በቅርበት የሚገኝ በመሆኑ በርካታ ምርቶችን በአንዴ ገዝቼ ለትራንስፓርት የምናወጣውን ገንዘብ እንዲቀንስ አስችሎኛል"። ሲሉ ገልጸዋል ። ቀደም ብሎ በተለጠፈው ዋጋ ዝርዝር ውጭ የመሸጥ ችግሮችና ጥራት የሌላቸው ምርቶችን የማቅረብ ችግሮች ሙሉ ለሙሉ መፈታታቸውንም ወ/ሮ ሄለን ጨምረው ገልጸዋል ።
ነዋሪታቸው በጎፋ ካምፕ የሆኑት ወ/ሮ አስቴር ጋዲሳ የገበያ ማእከሉ ላይ የፈለግኩትን የአትክልትና ፍራፍሬ አይነቶች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብልኝ በመሆኑ ሁሉንም አስቤዛየን የማደርገው በዚሁ ነው በተለይ በየቀኑ የምንጠቀምባቸው ሽንኩርትና ቲማቲም ሌሎች የግብርና ምርቶችን በ20 ብር ባላነስ ቅናሽ በመግዛቴ ተጠቃሚ ሆኛለሁ ሲሉ ገልጸዋል ።
#ንፋስ_ስልክ_ላፍቶ_ወረዳ_06_ኮሙኒኬሽን
12/07/2018
March 21, 2026 109






