ከአንገትህ በታች ሙሉ በሙሉ ሽባ ሆነሀል። የቤተሰቦቼን ሕይወት በጭካኔ ስትቀጥፍና ዓለማችንን ስታናጋ… — Jafer Books 📚 — TG.ME

"ከአንገትህ በታች ሙሉ በሙሉ ሽባ ሆነሀል። የቤተሰቦቼን ሕይወት በጭካኔ ስትቀጥፍና ዓለማችንን ስታናጋ ያላሰብከው ትልቁ ነገር፤ አንድ ቀን እንዲህ ባለ ሁኔታ በእኔ እጅ ላይ እንደምትወድቅ ነበር። አሁን በዚህ ሰዓት በቀላሉ ሕይወትህን ልነጥቅህና ልገድልህ እችል ነበር፤ ነገር ግን ሞት ላንተ እጅግ ትልቅ ስጦታና እረፍት ነው።" ንግግሬን በመቀጠል እንዲህ አልኩት፦

"ከዛሬ ጀምሮ የገዛ አካልህ ላንተ ዘላለማዊ እስር ቤት ይሆንሀል። መብላት፣ መጠጣት፣ አልፎ ተርፎም መጸዳዳትን... እነዚህን መሰረታዊ ነገሮች በሙሉ በሌላ ሰው እርዳታ ብቻ የምታደርግ ትሆናለህ። አባቴና ወንድሜ አሁን መቃብር ውስጥ ናቸው፤ አንተ ደግሞ በሕይወት እያለህ በዚህ አልጋ ላይ መቃብርህን ትሰራለህ።"

በዚህ ሰዓት በዓይኖቹ አጅግ ተለማመጠኝ። በዚህ የሚማጸን እይታው፦ "እባክህን ይበቃኛል ግደለኝ"የሚል ይመስላል።.....
❤19👍6🔥1
August 28, 2026 4.8K 7