ስለ ታይም ትኬት ለማብራራት ያክል ሀሳቡ ብዙዎቻችን ምርትና አገልግሎታችንን መሽጥ እንፈልጋለን። በተመሳሳይ…

ስለ ታይም ትኬት ለማብራራት ያክል
ሀሳቡ ብዙዎቻችን ምርትና አገልግሎታችንን መሽጥ እንፈልጋለን። በተመሳሳይ የምንፈልገው አገልግሎት ሲኖር ቀጠሮ ይዘን ሰዓታችን ሳይባክን እንደ ደረስን መስተናገድ እንፈልጋለን።
ስለዚህ አገልግሎት የሚሰጡ ግለሰቦች/ድርጅቶች የሚሰጡትን አገልግሎት በቀጠሮ ማግኘት ብንችል ብላችሁ አስቡት።
መፍትሄው አገልጋዪ ታይምትኬት ላይ አንድ ሊንክ ይኖረዋል።አገልግሎት መስጠት የሚችልበትን ሰዓት ያስቀምጣል። አገልግሎት ፈላጊዎች ደግሞ በሊንኩ ገብተው ቀጠሮ ያስይዛሉ ማለት ነው።
ለምሳሌ እኔን ለማግኘት የፈለገ ሰው ከስር ባለው ሊንክ ገብቶ ቀጠሮ አስይዞ የምሰጠውን አገልግሎትና ምርት ማወቅ ይችላል ማለት ነው።
ወይም ደግሞ አበባ መግዛት የፈለገ Habu Flower በሚኖራት ሊንክ ገብቶ ያዛታል ማለት ነው።
ይሄ ካልበቃ ደግሞ ዶክተር Seid Arage ጋር መሄድ የፈለገ የሱን ክፍት ሰዓት አይቶ ቀጠሮ መያዝና በቀጠሮው መሰረት በቦታው ተገኝቶ መገልገል ይችላል ማለት ነው።
የዶክተር Hawlet Ahmed ምክር ያስፈልገው ሰዓቷን book አድርጎ በሚመቻት ሰዓት ቀጠሮ ይዞ አገልግሎቷን ማግኘት ይችላል ማለት ነው፡።
ከላይ ለምሳሌ የተቀመጡት ሁሉንም አገልግሎቶች ለማሳየት ያክል ነው። ዌብሳይቱ በየቀኑ እየተሻሻለ ሲሆን በቅርቡም የሞባይል አፕ ይኖረዋል።
ሀሳብ አስተያየቶች ይበረታታሉ። ለጊዜ ዋጋ የሰጠ ጊዜም ዋጋ ይሰጠዋል። በጊዜ ለሚቀልደው ግን ጊዜ ቀልድ እንደማያውቅ ንገሩት፡፡
መልካም ምሽት
👍3❤1
October 6, 2026 366 1