ከቅጥር ስራ ወደ ስልጠና መስጠት ስመጣ የሺዎች ዶላር ክፍያ ስራ ትተህ እንዴት አስተማማኝ ወዳልሆነ እና በብር ስራ ትጀምራለህ የሚል ጥያቄ ቀላል ከማይባል ሰዎች ይቀርብልኝ ነበር፡፡ ይህን ስልጠና መስጠት በገንዘብ ከተለካ ለጊዜው ከቅጥር ስራ ከሚገኘው ያነሰ ገንዘብ የሚያስገኝ ቢሆንም በሚከተሉት ጠንካራ ምክንያቶች ተመራጭ አድርጌዋለው፡፡
1) በተፅኖ ከተለካ የቅጥር ስራ የትላልቅ ሀብታሞችን ስራ ማሳለጥ ሲሆን ይህ ስልጠና የብዙ የደሀ ልጅ የሀገሬን ልጆች ቢያንስ በዶላር ተከፋይ የሚሆኑበትን ክህሎት ማስታጠቅ በመሆኑ ለሀብታም ሀብት ለመጨመር ከመልፋት ለደሀ ልጆች የተሻለ ዳቦ እድል መፍጠር ስለሚበልጥ፡፡
2) በሂደት ከሰልጣኞቹም ጋር ትስስር እየፈጠርን ትልቅ በባለሙያዎች ባለቤትነት ላይ የተመሰረተ የአይቲ ተቋም መጠንሰስን ስለሚያስችል፡፡
3) አሜሪካ ፤ ካናዳ ፤ ዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ እና ሀገር ውስጥም ያሉ ትልልቅ አለማቀፍ የሶፍትዌር ካምፓኒዎች ውስጥ ለአመታት ስሰራ የገነባዋቸውን መልካም ትውውቆች በመጠቀም ለሰልጣኞች ከክህሎት በዘለለ የስራ እና የልምምድ አውድ መፍጠርን በማለም፡፡
4) ብዙ የሚችሉ ሰዎች ገበያው ውስጥ ሲፈጠር በሂደት ለሀገር አዲስ የስራ እድል ከባህር ማዶ ሀገራችን ላይ ሆነን እያመጣን ኢኮኖሚው ላይ የበኩላችንን ጠጠር ለማኖር
5) እገዛ የሚሹ ሰዎችን እገዛ ለማድረግ የራስ ስራ እድል ስለሚሰጥ
በሚል ምክንያት ከቅጥር ወደግል ስራ መቀየርን ወሰንኩ፡፡ በምስሉ ላይ የተቀመጠው ጥያቄ ከነዚህ ከላይ ከተዘረዘሩት መሰረታዊ አላማዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን የስራ እና ኢንደስትሪ ልምምድ እድልን ይመለከታል፡፡ በዚህ ረገድ የመጨረሻው ቀጣሪ ድርጅቴን ስለቅ በተሻለ ሁኔታ ዳግም እንደምንገናኝ ለExcellerent Solutions, Ethiopia Delivery Center, Country Director ነግሬው ነበር፡፡
በኔም በሱም ቢዚ መሆን እና ሁኔታዎች አለመገጣጠም እስካሁን በደንብ አልሄድንበትም ነበር፡፡ ትላንት በምስሉ ላይ የምታዩትን ጥያቄ ከአንድ እጩ አመልካች ሲቀርብ ደረቅ መልስ ከመመለስ ወደ ተግባር መግባት ይሻላል በሚል ለመጀመር ያክል ከ Excellerent Solutions, Ethiopia Delivery Center, Country Director ጋር ዛሬ በስልክ ሀሳቡን አወራሁለት፡፡
በጣም ደስተኛ ሆኖ እረፍት ላይ እንደሆነና ከ10 ቀን በኋላ ወደ ስራ እንደሚገባ ሲመለስም የመጀመርያ የማኔጅመንት ስብሰባ ላይ የቀድሞ ሰራተኛችን በሆነ ግለሰብ የተመሰረተ Radiant Tech Solutions የሚባል ተቋም አብሮ የመስራት ስምምነት እንዲኖረን ማኔጅመንቱን አወያይቶ እንደሚያሳውቀኝ እና ከ15 ቀን በኋላ እንዳስታውሰው ነግሮኛል፡፡
ይህ እድል ለራዲየንት ቴክ ሶሉሽንስ ሰልጣኞች የinternship እና የስራ ቅጥር እድልን ያካተተ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ሰልጣኞች በሌላ ፍሬምዎርክም ጭምር የቀድሞ ልምድ እንዳላቸው ነግሬው ከ.NET በተጨማሪ ባላቸው ፊልድም እድል ማመቻቸት ፍላጎቱ እንደሆነ ነግሮኝ የማኔጅመንት ውሳኔውን እንድጠብቅ አሳውቆኛል፡፡
ይህ ለራዲየንት ቴክ ሶሉሽንም ሆነ ለሰልጣኞቻችን መልካም ዜና ነው፡፡ የኤግዘለረንት ሶሉሽንስ ማኔጅመንት የምንፈልገውን ውሳኔ እንደሚወስኑ ተስፋችን ነው፡፡