የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በጋምቤላ ክልል ተቋርጦ የነበረውን አገልግሎት ድጋሚ ለማስጀመር የቅድመ… — Jimma immigration (ICS Ethiopia) — TG.ME

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በጋምቤላ ክልል ተቋርጦ የነበረውን አገልግሎት ድጋሚ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን ገለጸ።

ሀምሌ 25/2017 ዓ.ም

በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ የተመራ የልዑካን ቡድን ከክልሉ አስተዳደር ጋር ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ወቅት በጋምቤላ ክልል ተቋርጦ የነበረው አገልግሎት በቅርቡ ስራ እንደሚጀምርና ለዚህም አሰራሩን የማዘመን፥ የመሰረተ ልማት የማሟላት እና በሰው ሃይል የማደራጀት ተግባራት እየተጠናቀቁ ነው ብለዋል ።

ህገወጥ አሰራሮችን በማስቀረት ዜጎች ፓስፖርትን ጨምሮ ሌሎች የኢሚግሬሽን አገልግሎቶችን በተሻለ ሁኔታ እንዲያገኙ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል አቶ ቢቂላ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ተቋርጦ የነበረውን አገልግሎት በተሻለ አሰራር በድጋሚ ለማስጀመር እያደረገ ባለው ጥረት የክልሉ መንግስት ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። ተቋሙ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለዜጎች እንዲሰጥ ክልሉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል።

በጋምቤላ ክልል የሚገኙ የድንበር ኬላዎች ቁጥጥር ማጠናከር እና ከክልሉ ተወላጅ ስደተኞችና ስደት ተመላሾች ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት በሚቻልበት ጉዳይ ላይም ውይይት አካሂደዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
——
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/ics_ethiopia
❤19
August 1, 2025 3.8K 6