ርቀትህን ጠብቅ...በማኅበራዊ ግንኙነትህም ሆነ በጓደኝነት ሕይወት ውስጥ መሄጃና መድረሻ የሌለህ ይመስል በሰው… — Ibnu berkelle (ኢብኑ በርከሌ) — TG.ME

ርቀትህን ጠብቅ...በማኅበራዊ ግንኙነትህም ሆነ በጓደኝነት ሕይወት ውስጥ መሄጃና መድረሻ የሌለህ ይመስል በሰው ላይ አትጣበቅ። ሰዎችን በጣም አትቅረባቸው ይውጡሃል፣ በጣምም አትራቃቸው ይተፉሃል። ለረጅምና ዘላቂ የጓደኝነት ግንኙነት በትስስራችሁ መካከል መጠነኛ ክፍተት ተው። ሰውን ስትወድ ውዴታህን በልክ አድርግ። ሰው ሰው መሆኑን እወቅ።

ሰዎች በጣሙን ከቀረብካቸዉና ካበዛኸው ያለ ማስጠንቀቂያ ሊያወርዱህም ሊያዋርዱህም ይችላሉ። ያኔ «እኔው ነኝ ያበዛሁት፣ የቀበጥኩት፣ ራሴን የጣልኩት…» ከማለትህ በፊት ርቀትህን ጠብቅ።
👍3❤1
September 3, 2026 25 1