🌼 እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! 🌼
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ካምፓስ የተማሪዎች ህብረት ለመላው የካምፓሳችን ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች (Staff) እንዲሁም ለቤተሰቦቻችሁ በሙሉ እንኳን ለ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ ልባዊ የመልካም ምኞት መልእክቱን ያስተላልፋል!
አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የትልቅ ስኬት ዘመን እንዲሆንልን ከልብ እንመኛለን።
በአዲሱ ዓመት ትኩረት ሰጥተን የምንመኛቸው መልካም ነገሮች፦
ለተማሪዎቻችን፡ አዲሱ ዓመት የትምህርት ዘመናችሁ የተሳካ፣ በምታጠኑት ትምህርት የላቀ ውጤት የምታስመዘግቡበት፣ አዳዲስ እውቀቶችን የምትቀስሙበት እና ህልማችሁን የምታሳኩበት ብሩህ ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
ለካምፓሱ መምህራን እና ሰራተኞች (Staff)፡ ትውልድን በመቅረጽ እና ምቹ የመማሪያ አከባቢን በመፍጠር ለምታደርጉት አበረታች እና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ለምታደርጉት ጥረት ጥልቅ አክብሮታችንን እየገለጽን፤ አዲሱ ዓመት ስኬት፣ የጤና እና የደስታ ዓመት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
በ2019 ዓ.ም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ካምፓስ የተማሪዎች ህብረት የተማሪዎችን መብት ለማስጠበቅ፣ የመማር ማስተማር ሂደቱን ይበልጥ ለማሳለጥ እንዲሁም በካምፓሳችን ውስጥ ጤናማ እና አብሮነት የሰፈነበት ማህበረሰብ ለመፍጠር ከመቼውም ጊዜ በላይ ከሁሉም አካላት ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ በዚሁ አጋጣሚ ቃል ሊገባ ይወዳል።
ዓመቱ የሰላም፣ የዕድገት እና የአንድነት ዓመት ይሁንልን!
መልካም አዲስ ዓመት! 🌼
---
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ካምፓስ የተማሪዎች ህብረት
📍 ሀዋሳ፣ ሲዳማ፣ ኢትዮጵያ












