የማለዳ መልእክት (47)
~
ልጅ ትልቅ ሃብት ነው። እንዲያውም ከልጅ በላይ ሀብት የለም። ህንፃ ቢደረደር፣ ሃብት ቢትረፈረፍ ያለ ልጅ ጣእም የለውም። የልጅን ኒዕማ የሚያቃልለው ወይ ህይወት ያለ ልጅ ምን ያክል ባዶ እንደሆነች የሚረዳበት የእድሜ ክልል ላይ ያልደረሰ ነው። ወይ ደግሞ አእምሮው በሌሎች መጥፎ አስተሳሰብ የተበከለ አካል ነው። እንጂ በተትረፈረፈ ሃብት ውስጥ ብትሆን እንኳ ያለ ልጅ ህይወት ጣእም አልባ ናት። የአላህ ነብይ ዘከሪያ የነበራቸውን ስሜት እና የሰጣቸውን ፈረጃ አላህ እንዲህ ሲል ይገልፀዋል:-
{ وَزَكَرِیَّاۤ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥ رَبِّ لَا تَذَرۡنِی فَرۡدࣰا وَأَنتَ خَیۡرُ ٱلۡوَ ٰرِثِینَ (89)
"ዘከሪያንም፡ 'ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ፡፡ አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ' ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡''
فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ وَوَهَبۡنَا لَهُۥ یَحۡیَىٰ وَأَصۡلَحۡنَا لَهُۥ زَوۡجَهُۥۤۚ إِنَّهُمۡ كَانُوا۟ یُسَـٰرِعُونَ فِی ٱلۡخَیۡرَ ٰتِ وَیَدۡعُونَنَا رَغَبࣰا وَرَهَبࣰاۖ وَكَانُوا۟ لَنَا خَـٰشِعِینَ (90) }
"ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ የሕያንም ሰጠነው፡፡ ለእርሱም ሚስቱን አበጀንለት፡፡ እነርሱ በበጎ ሥራዎች የሚቻኮሉ ከጃዮችና ፈሪዎች ሆነው የሚለምኑንም ነበሩ፡፡ ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ፡፡" [አልአንቢያእ፡ 89-90]
በርግጥ ትልቁ ነገር እንዲሁ ልጅ መኖሩ ብቻ አይደለም፣ አስተዳደጉ ሲያምር ነው ልጅ የዓይን ማረፊያ፣ የዱንያ ምርኩዝ፣ የኣኺራ ስንቅ የሚሆነው። ስለዚህ ልጆቻችን ከየትኛውም ሃብት በላይ ናቸውና አጥብቀን እንድከምላቸው።
ውለዱ፣ ክበዱ። አስተዳደጋቸው ላይ ትኩረት ስጡ። የሌላችሁ አላህ ልጅ ይስጣችሁ። ያልተሰካላችሁ አላህ ስብራታችሁን ጠግኖ በኣኺራ ይካሳችሁ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል አወል 05/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Forwarded fromIbnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور

1August 19, 2026 114