ሙስሊም ወንድሞቼ ፣ ጊዜው ሳያልፍ እንንቃ!
ያ አላህ! ጉዳዩ እየከበደና እያሳሰበ መጥቷል። ሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ለተለያዩ ፊርቆችና አስተሳሰቦች እየተጋለጠች ነው። አንዳንድ ቡድኖችና እንቅስቃሴዎችም በሕዝቡ መካከል እየተስፋፉ ሲሆን፣ በተለይም ወጣቶችንና ሕፃናትን ማነጣጠራቸው እየጨመረ ነው።
በቅርብ ጊዜም ከአህሉስ-ሱና ወልጀማዓ አስተምህሮ ፍፁም የሚለያዩ ቡድኖች፣ ከእነሱም መካከል ሺዓ፣ አሕመዲያ እና ሌሎችም በአንዳንድ አካባቢዎች እየተስፋፉ እንደሚገኙ እናስተውላለን። በተለይም በባቲና በአካባቢዋ የተለያዩ የትምህርትና የዳዕዋ እንቅስቃሴዎች እየተካሄዱ መሆናቸው ትኩረታችንን ይሻል።
በተለይ ልንጠነቀቅ የሚገባን ሕፃናትና ወጣቶች ላይ የሚደረገው ትኩረት ነው። አንዳንድ ወገኖች ትምህርት ቤቶችን፣ ማዕከላትንና የትምህርት ተቋማትን በመክፈት ሕፃናትን ገና ከልጅነታቸው ከ kg ጀምሮ ለማስተማር እየሰሩ ነው።
እንግዲህ ራሳችንን መጠየቅ ይገባናል፦
ልጆቻችን እና ወጣቶች ምን እየተማሩ ነው?
ምን ዓይነት እምነትና አስተሳሰብ እየተቀበሉ ነው?
ትምህርታቸውን የሚከታተልና አቅጣጫ የሚሰጣቸው ማን ነው?
ወንድሞቼና የተከበራችሁ ወገኖቼ ሆይ!
ከሀገራችን ጫፍ እስከ ሌላኛው ጫፍ ድረስ፣ የአህሉስ-ሱና ወልጀማዓ ተከታዮች ሆይ፣ የአካባቢያችን ሰዎች ሆይ፣ በተለይም የባቲ ነዋሪዎች ሆይ!
የልጆቻችን የወጣቶችን የራሳችንንእምነት መጠበቅና የአላህን መጽሐፍ እና የነቢዩን ﷺ ሱና ማስተማር ታላቅ ኃላፊነት ነው።
ይህንንም በዘፈቀደ ግጭት፣ በስድብ ወይም ሌሎችን በማዋረድ ሳይሆን፣ በዕውቀት፣ በጥበብ፣ በትክክለኛ ትምህርት፣ በግንዛቤ ማስጨበጥ እና ማህበረሰባችንን በቁርአን፣ በሱናና በትክክለኛ የእስልምና እምነት ማጠናከር ነው።
ማህበረሰባችንን በቅርብ ልንከታተል፣ ምን እንደሚማሩም ልናውቅ ይገባል። በራሳችን ትምህርት ቤቶችና የእስልምና ማዕከላት ውስጥም ጠንካራና ጠቃሚ ትምህርት እንዲያገኙ ልንጥር ይገባል።
ይህም ቁርአንን፣ ትክክለኛ የአቂዳ ትምህርትን፣ ፊቅህን፣ መልካም ሥነ-ምግባርንና የዓረብኛ ቋንቋን ያካተተ መሆን አለበት።
ሌሎች ሰዎች ቦታውን እንዲይዙ ከፈቀድን በኋላ፣ ሐሳቦቻቸው ስለተስፋፉ ብቻ ማማረር መፍትሔ አይሆንም።
ስለዚህ ኃላፊነታችንን እንወጣ። ማህበረሰባችን ከሌሎች ዘንድ ከመማራቸው በፊት እኛ እናስተምራቸው። የተሳሳቱ አስተሳሰቦችንም በዕውቀት፣ በማስረጃና በጥበብ እንመልስ።
ኢንሻአላህ፣ እነዚህ ቡድኖች ምን እንደሆኑ፣ መሠረታዊ ሐሳቦቻቸውና እምነቶቻቸው ምን እንደሆኑም በማስረጃና በታማኝ ምንጮች ላይ በመመስረት አብራራለሁ፤ ዓላማዬም ሙስሊሙ ስለ ዲኑ በቂ ዕውቀት እንዲኖረውና በጉዳዮች ላይ በግልጽ እውቀት እንዲቆም ነው።
አላህ ሆይ! ሀገራችንንና ማህበረሰባችንን ጠብቅ። እኛንና እነርሱን በቁርአንና በሱና ላይ አጽና። ዑለማዎቻችንን፣ ዳዒዎቻችንንና መምህራኖቻችንን ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ እርዳቸው። ከቀናው መንገድ የራቁትንም ወደ እውነት ምራቸው።
አላህ ሆይ! የሙስሊሞችን ልጆች ጠብቅ፣ እምነታቸውን ጠብቅ፣ ወደ እውነትና መልካም ሥራ የሚጠሩ ዳዒዎች አድርጋቸው።
አሚን!
=
አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ
https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
Forwarded fromIbnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Telegram
አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ
قال الإمام مالك ((لايصلح آخر هذه الأمة إلا بماصلح به أولها))

August 16, 2026 172